Connect with us

ፍርድ ቤቱ የአቶ ልደቱ አያሌውን ፋይል ዘጋ

ፍርድ ቤቱ የአቶ ልደቱ አያሌውን ፋይል ዘጋ
Photo: Social Media

ህግና ስርዓት

ፍርድ ቤቱ የአቶ ልደቱ አያሌውን ፋይል ዘጋ

ፍርድ ቤቱ የአቶ ልደቱ አያሌውን ፋይል ዘጋ
~ የዋስትና ጥያቄ ሊያቀርቡ ይችላሉ ብሏል፣
***

የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት በአቶ ልደቱ ላይ ክስ እስከሚመሰርት መርማሪ ፖሊስ እንዲሰጠው የጠየቀውን ተጨማሪ ጊዜ ውድቅ በማድረግ ነው መዝገቡን የዘጋው።

አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ፖሊስ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን ገልፆ አቃቤ ህግ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ 14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የፖሊስ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም ሲል ውድቅ አደረገ።

ፍርድ ቤቱ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ መዘጋቱን ገልፆ አቶ ልደቱ አያሌው በሌላ መዝገብ የዋስትና ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ አዟል።

ለአራተኛ ጊዜ በቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ልደቱ አያሌው ”ፍርድ ቤቱ የጤናዬን ሁኔታ ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት፣ ከዚህ በፊት ያቀረብኩት የህክምና ማስረጃ የልብ ህመምተኛ መሆኔን ተከትሎ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭ እንደሚያደርገኝ ተጠቅሶ የተፃፈ ቢሆንም፥ በፖሊስ ጣቢያ የኮቪድ-19 ምርመራ አልተደረገም፣ ጤናዬን ከግምት ውስጥ ያስገባ ርቀትን የጠበቀ አያያዝ አልተደረገልኝም፣ በተጓዳኝ ደግሞ በአንድ መፀዳጃ ቤት 50 እስረኞች እንደሚጠቀሙና ይህም ለጤናዬ አደጋ ነው‘ ብለዋል።

”ፖሊስ እስከ ዛሬ ሲያከናውን የነበረው ምርመራ አዲስ ውጤት ያልታከለበት፣ አስተባብረሃቸዋል የተባሉ ተባባሪዎች ያልተያዙበት እና ምስክሮቼ ያልቀረቡበት ነው‘ ሲሉ መቃወሚያ አሰምተዋል።

ፖሊስም እስካሁን ሲያከናውን የነበረው ምርመራ በእጃቸው ላይ የነበሩ የስልክ መልዕክቶችን እንዲሁም በእጃቸው ላይ የተገኘ የሽግግር መንግስት መመስረቻ ሰነዶች ውጤትን በመዝገቡ ማካተቱን ገልፆ፥ ይሁንና ”ምርመራዬን አጠናቅቂያለሁ፣ ይህም መዝገቡንም አቃቤ ህግ መርምሮ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ‘ ሲል ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም ”በዚህ መዝገብ ላይ ምርመራ መጠናቀቁን በመግለፅ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ አንቀፅ 59 1 እና 2 መሰረት ያቀረብከው ጥያቄ አግባብነት የሌለውና ያጠናቀከው መዝገብ ተጨማሪ ጊዜ የማያሰጥ ነው፣ ጥያቄህም የህግ አግባብነት የለውም‘ ሲል ውድቅ አድርጎበታል።

ይሁንና በዛሬው ዕለት በሁለት ጠበቃ ተወክለው የቀረቡት አቶ ልደቱ አያሌው የጠየቁት የዋስትና ጥያቄ በዚህ የተዘጋ መዝገብ ሳይሆን በሌላ መዝገብ ማቅረብ ይችላሉ ሲል የመርማሪ ፖሊስ መዝገብን መዝጋቱን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top