Connect with us

ታከለ ኡማ መልስ ሰጡ!

ታከለ ኡማ መልስ ሰጡ!
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

ታከለ ኡማ መልስ ሰጡ!

#ታከለ_ኡማ መልስ ሰጡ!

“በህገወጥ መንገድ የተሰጠ ምንም አይነት ቤት የለም”

ኢ/ር ታከለ ኡማ የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ከመሬት ወረራ እና ከህገወጥ የኮንደምኒየም እደላ ጋር በተያያዘ ኢዜማ በትላንትናው ዕለት ይፋ ያደረገውን ጥናት በተመለከተ በፌስ ቡክ ገጻቸው የሰጡት ምላሽ እነሆ:-
***

ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ተገቢው ቦታ ላይ ባልገኝም ከዚህ የመጓተት ፖለቲካ አስተሳሰብ መውጣት አለመቻል ግን ትልቅ ህመም እንደሆነ ይሰማኛል።

የመሬት ወረራን በተመለከተ ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ጠንካራ የሆነ እርምጃ ስንወስድበት የቆየንበት ጉዳይ ነው። በተለያዩ ጊዜዎች የወሰድናቸው እርምጃዎችም ህያው ምስክሮች ናቸው።

እኛ ህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል እርምጃ ስንወስድ የዛሬ ተቺዎች የሰብአዊ መብት ተነካ፣ ዜጎች ተፈናቀሉ ብለው ዘመቻ ከከፈቱብን ውስጥ ነበሩ።

ለ20ሺህ አርሶአደሮች የተሰጡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች በተመለከተም ከአንድ አመት ተኩል በፊት በካቢኔ የተወሰነና የተተገበረ ነው። በድብቅ የተተገበረም ሳይሆን በመንግስት ሚዲያም በይፋ የተገለፀ ነበር።

ከመሬታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ከወደቁ በራሳቸው መሬት ላይ በተሰራ ህንጻ ዘበኛ እና ተሸካሚ ሆነው ከቀሩ 67 ሺህ አባወራዎች መሃል የከፋ ችግር ላይ ለወደቁት 20 ሺህ ኮንዶሚንየም ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም። ከዚህ ውጭ በህገወጥ መንገድ የተሰጠ ምንም አይነት ቤት የለም።

ይህ ሥራችን በተደጋጋሚ በይፋ ስንናገር እንደነበረው የምናፍርበት ሳይሆን የምንኮራበት ነው። በግፍ የተገፋን፣ በግፍ ከመሬቱ የተፈናቀለን አርሶ አደር መካስ ያኮራናል!

በዙሪያዋ ካሉት አርሶ አደሮች ጋር በፍቅር ተሳስባ የምትኖር የተሰናሰለች ከተማ እንጂ በዙሪያዋ ካሉት ህዝቦች ጋር የተቀያየመች ከተማ እንድትኖር አንሻም ነበርና። ይህ ደግሞ የከተማዋ ነዋሪዎች ፍላጎት መሆኑንም እንገነዘባለን።

አንድም ቀን በግፍ ለተፈናቀሉ አርሶአደሮች የመቆርቆር ስሜት አሳይቶ የማያውቅ ቡድን ዛሬ የአርሶአደሮችን ጉዳት ለተቀባይነት ማግኛ መጠቀሚያ ሲያደርገው ማየት ያሳዝናል።ነገር ግን በሃሰተኛ እና በተጋነነ መረጃ ጠንካራ መምሰል እንጂ መሆን አይቻልም።
በሀሰተኛ መረጃ ድካማችንና ስራችንን ለማጠልሸት ቢሞከርም ስራችን ይናገራልና ፍርድ የህዝብ ነው!

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top