Connect with us

ኢዜማ ወደፍርድ ቤት አመራ

የአማፂያንን የጦር አውርድ ለመግታት ዜጎች በጋራ መቆም ይኖርብናል!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ

ዜና

ኢዜማ ወደፍርድ ቤት አመራ

ኢዜማ ወደፍርድ ቤት አመራ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በ28 ምርጫ ወረዳዎች ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የተደረገው ምርጫ በድጋሚ እንዲደረግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ አስገባ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች የተደረገው ምርጫ ላይ ከድምጽ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ፥ ከቀበሌ እስከ ክልል ባሉ የገዢው ፓርቲ አመራሮች፣ ከቀበሌ ሚሊሻ እስከ ክልል ልዩ ኃይል ድረስ ባሉ የፀጥታ አስከባሪዎች፣ የምርጫ ጣቢያ የምርጫ አስፈጻሚዎች እና ለጊዜው ማንነታቸውና ሕጋዊ የሥራ ኃላፊነታቸው በግልጽ ያልታወቀ ግለሰቦች በድምጽ አሰጣጥ ሂደት እና በምርጫው ውጤት ላይ እጅግ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደሩ እና የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥትን፣ የምርጫ አዋጅን እና ምርጫ ቦርድ ያወጣቸውን መመሪያዎች በቀጥታ የሚጻረሩ ተግባሮች መፈፀማቸውን በመጥቀስ የሰው፣ የሰነድ፣ የቪድዮ እና የምስል ማስረጃዎችን በማያያዝ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም ቅሬታ አስገብቶ ነበር።

ኢዜማ ዛሬ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባስገባው አቤቱታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቀረቡለትን ቅሬታዎች እና ማስረጃዎች በአግባቡ ሳይገመግም ውሳኔ ማስተላለፉን ጠቅሶ ፍርድ ቤቱ ከበቂ በላይ ማስረጃ በቀረቡባቸው 28 ምርጫ ወረዳዎች ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ጠይቋል።

የኢፌደሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታውን ተቀብሎ ጉዳዮን ማየት ለመጀመር ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል።

የኢዜማ ጠበቆች ቡድን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኢዜማ ቅሬታ ያስገባባቸውን 68 ምርጫ ወረዳዎች እና ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረበባቸውን 28 የምርጫ ወረዳዎች በተመለከተ ማብራሪያ የሚሰጥበት ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በኢዜማ ዋና ጽሕፈት ቤት መስፍን ወልደማሪያም አዳራሽ ይሰጣል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top