Connect with us

ጃዋር መሀመድ የፖለቲካ እስረኞች ነን አለ

ጃዋር መሀመድ የፖለቲካ እስረኞች ነን አለ
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

ጃዋር መሀመድ የፖለቲካ እስረኞች ነን አለ

እነ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ስምንት ተጠርጣሪዎች ቀሪ የዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር ለመስማት የተቀጠረ ቢሆንም ከ4ኛ እስከ 9ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ውጤት ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዪት ስላልመጣ ለነሃሴ 22 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ።

በችሎቱ የተገኙት አቶ ጃዋር መሀመድ ውጭ ሀገር ከሚገኙት ልጃቸው እና ባለቤታቸው ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ አንድ ጊዜ ብቻ መገናኘታቸውን በመግለፅ በድጋሚ እንዲገናኙ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም በዚህ እና በተነሱ ሌሎች አቤቱታዎች ላይ በቀጣይ ቀጠሮ ትዕዛዝ እሰጥበታለሁ ማለቱን ፋና ዘግቧል።

በዚሁ ጉዳይ የኢሳት ዘገባ እንዲህ ይላል። አቶ ጃዋር መሀመድ እኛ የፖለቲካ እስረኞች በመሆናችን አቃቢያን ህግ ከፖለቲከኞች ጋር ተነጋግራችሁ ውሳኔ እንዲሰጥበት አድርጉ ። ፖለቲከኞች ምርጫው እስኪያልፍ ድረስ በእስር ቤት ውስጥ እንድንቀመጥ ፈልገው ከሆነ ቁርጡን ንገሩን ፍ/ቤት አታመላልሱን ። ሲል ለችሎቱ ተናግሯል።

በቀለ ገርባ በበኩሉ እኛን ማሰር ህዝብን ከህዝብ ማራራቅ ነው። አገራዊ የፖለቲካ መፍትሄ የሚመጣው ፖለቲከኞች ተቀራርበው ሲነጋገሩ ነው። ሲል ለችሎቱ አስረድቷል። አቶ በቀለ አያይዞም ይህን ቀን በጉጉት ስጠብቀው ነበር። የብዙሀን መገናኛ በእኔ ላይ ዘምተውብኛል። ማህበራዊ ሚዲያ እኔን ወንጀለኛ አድርገው ነው የሚከሱኝ። አሁን ይሄው ቀረብኩላቸው ። በሉ ማስረጃዎችን ሰብስቡ እና አስወስኑብኝ። እኔም ንፅህናዬን ማሳየት እፈልጋለሁ። ብሏል።

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top