Connect with us

በአሜሪካ ኮንግሮስ የብላክ ኮከስ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ

በአሜሪካ ኮንግሮስ የብላክ ኮከስ ግድቡን በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት ባለደርሻ አካላትን በማሳተፍ እንዲሰራ ጠየቀ
Photo: Social Media

አለም አቀፍ

በአሜሪካ ኮንግሮስ የብላክ ኮከስ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ

በአሜሪካ ኮንግሮስ የብላክ ኮከስ ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የአፍሪካ ህብረት በአህጉሪቱ የሚገኙ ባለደርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ ሰላማዊ እልባት ለመስጠት እንዲሰራ ጠይቋል።

ኢትየጵያ ግብፅና ሱዳን በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ በመመስረት የሚያደርጉት ድርድር ሰላማዊ እንዲሁን የሚያበረታታ መሆኑንም በአሜሪካ ኮንግሮስ ብላክ ኮከስ አስታውቋል፡፡

ሶስቱ ሃገራት በግደቡ ዙሪያ የሚያደርጉት ድርድር በእውነተኛነት፣ በጋራ ተጠቃሚነት እና በአለም አቀፍ ህጎች ላይ ሊመሰረት እንደሚገባውም አመልክቷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በግድቡ ዙሪያ አሜሪካን ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት ሀገራትበእና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ስል ጉዳዩ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁሟል።

በተለይ ሶስቱ ሃገራት እኤአ በ2015 የደረሱበትን ስምምነት ሊያከበሩ እንደሚገባቸውም አሳስቧል፡፡
ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በጎ ጎን አለው ያለው ኮንግሮንሱ ሶስቱ ሃገራት በምግብ ፣ በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እና በንፁህ ውሃ መጠጥ እራሳቸውን ችለው ካደጉ ሃገራት ተርታ እንዲሰለፉ ይረዳልም ሲል ጨምሮ ገልጿል፡፡

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top