Connect with us

አዲሱ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የድረ ገጽ ገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ሥርዓት ሁሉም ዳያስፖራ አሳታፊ ያደርጋል

አዲሱ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የድረ ገጽ ገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ሥርዓት ሁሉም ዳያስፖራ አሳታፊ ያደርጋል-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል

ዜና

አዲሱ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የድረ ገጽ ገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ሥርዓት ሁሉም ዳያስፖራ አሳታፊ ያደርጋል

አዲሱ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የድረ ገጽ ገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ሥርዓት ሁሉም ዳያስፖራ አሳታፊ ያደርጋል-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል

( http://xn--www-snp.mygerd.com/)

ከሰሞኑ ይፋ የተደረገው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የድረ ገጽ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ሥርዓት ማንኛውንም ዳያስፖራ በማሳተፍ አሻራውን እንዲያሳርፍ የሚያስችል መተግበሪያ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታወቀ።

ዳያስፖራው በቦንድ የሚሳተፍበት ዲጂታል ቦንድ ግዥ ሥርዓት ለማበልጸግም በሂደት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ከሰሞኑ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ድረ ገጽ መተግበሪያ በኢትዮጵያዊያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በልጽጎ ይፋ ሆኗል።

መተግበሪያው በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሚኖሩበት ቦታ ሆነው እንደ አቅማቸው የፈለጉትን ገንዘብ መጠን ድጋፍ የሚያደርጉበት ድረ-ገፅ እንደሆነ ገልጸዋል።

ኤሌክትሪክ ኃይል በቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ በተሰኘ የወጣት ኢትዮጵያዊያን የቴክኖሎጂ ድርጅት ጋር በመተባበር በነጻ እንዲበለጽግ ማድረጉን ገልጸዋል።

በገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብሄራዊ ባንክና ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዕውቅና የተሰጠው http://xn--www-snp.mygerd.com/ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ድረ-ገጽ፤ በቀላልና አስተማማኝ መንገድ ከፈቃደኛ ለጋሾች ለግድቡ ገንዘብ ማሰባሰብ የሚያስችል እንደሆነ ጠቁመዋል።

ከዚህ በፊት በተለይም በአሜሪካ፣ ካናዳና አውሮፓ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለግድቡ ድጋፍ ለማድረግ በኤምባሲዎች በኩል ሲያካሂዱ መቆየታቸውን ገልጸው፤ ነገር ግን “አሰራሩ ምቹና ቀልጣፋ አልነበረም” ብለዋል።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን “ከሁለተኛው የግድቡ ውሃ ሙሌት በኋላ ድጋፍ ለማድረግ መነሳሳት አሳይተዋል” ያሉት አቶ አሸብር፤  የድጋፍ ማሰባሰቡን አሰራር ያዘመነ ድረ ገጽ መሆኑን ተናግረዋል።

ድረ ገጹ በኢትዮጵያ መረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በኩል እውቅና ያለውና ድጋፍ ሰጭውን የማያጠራጥር የድረ ገጽ ሥርዓት መሆኑን አብራርተው፤ “እስካሁን ያለው የገንዘብ ማሰባሰብ እንቅሰቃሴ አበረታች ነው” ብለዋል።

ድረ ገጹ የለገሰው ሰው ማንነትና የተለገሰውን ገንዘብ መጠን ማሳየት የሚችል እንደሆነ ገልጸው፤ ድጋፍ ለማድረግ የሚፈልግ ዜጋ ሁሉ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።

በድረ-ገፁ አማካኝነት የሚሰባሰበው ድጋፍ በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በተሰጠው ዘመን ባንክ ለግድቡ በተከፈተ የውጭ ምንዛሬ ሒሳብ ቁጥር በቀጥታ ገቢ የሚደረግ መሆኑንም ተናግረዋል።

ሌላው ድረ-ገፁ ግለሰቦች ገንዘብ ገቢ እንዲያደርጉ ሳይሆን በራሳቸው ስም ገንዘብ እንዲያሰባስቡ የሚያስችል ሲሆን፤ የሚሰበሰበው ገንዘብ ግን በቀጥታ በዘመን ባንክ የሕዳሴ ግድብ አካውንት ብቻ እንዲገባ የሚያድርግ መሆኑን አብራርተዋል።

ይህ መተግበሪያ ለአጭር ጊዜ ጥሩ መፍትሄ መሆኑን አንስተው፤ በቀጣይም ደግሞ በውጭ አገሮች የሚኖሩ ዜጎች በቦንድ ግዥ የሚሳተፉበት “ዲጂታል ቦንድ ስርዓት ገቢራዊ ለማድረግ በሂደት ላይ ነን” ብለዋል።(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top