Connect with us

የሀገሬን ጠቅላይ ሚኒስትር የዘለፈችው እንግሊዛዊት …

የሀገሬን ጠቅላይ ሚኒስትር የዘለፈችው እንግሊዛዊት
Photo: Social media

አስገራሚ

የሀገሬን ጠቅላይ ሚኒስትር የዘለፈችው እንግሊዛዊት …

የሀገሬን ጠቅላይ ሚኒስትር የዘለፈችው እንግሊዛዊት ላይ ሕግ ተገቢውን እርምጃ ይውሰድ፡፡
አየሁት ካለችው ራዕይ የእንግሊዝን ፓስፖርት የምትታመን የኢትዮጵያ ንግሥት ነኝ ባይ-እህተ ማርያም
ከስናፍቅሽ አዲስ

የእህተ ማርያምን ንግግሮች አድምጫለሁ ደጋግማም የሀገሬን መሪ ዶክተር አብይን ስትሰድብ ሰምቻለሁ፤ አንዲት እንግሊዛዊት በጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሰው ሀገር መሪን ከፍ ዝቅ የማድረግ መብት የላትም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደለመዱት ይቅርታ የማድረግ ሱሳቸው ቢያዛጋቸው እንኳን የሀገሬ መሪ የተሰደበብኝ ዜጋ ስለሆንኩ እኔ አልተዋትም፡፡ ህግ ተገቢውን ፍርድ እንዲሰጣት እጠይቃለሁ፡፡

ሴት ብሆንም እንዲች አይነት ወንድ ያከበረውን ሀገር ማዋረድ የምትፈልግ የሰው ሀገር ሰው አታሳዝነኝም፡፡ አንድ እንግሊዛዊት በሀገሬ ያሻትን ስታደርግ መሰንበቷና መኖሯ በራሱ ደህንነቱ ምን ሰርቶ እንደሚበላ እንድጠይቅ ያስገድደኛል፡፡ ወይም እጁ አለበት ለማለት እገደዳለሁ፡፡

ሴትየዋ ራዕይ አይቻለሁ ብትልም ያየችውን ራዕይ የእንግሊዝ ዜግነቷን ያህል አትተማመንበትም፡፡ ማርያም ተገልጻልኛለች እያለች ዋስትና ብላ የተማመነችው ግን በእንግሊዝ ፓስፖርቷ ነው፡፡ ሮምን የሚያብጠለጥሉ ደጋፊዎች ይዛ አውሮፓን እያሽሟጠጠች ባንዲራዋን የምትለብስላትን ሀገር ፓስፖርት ግን የኔ ልትለው አልቻለችም፡፡

የኢትዮጵያ ንግሥት መሆን የምትፈልገው በእንግሊዝ ፓስፖርቷ ዋስትና ነው፡፡ ዜግነቷን ያልቀየረችው ራዕይ ያየችላት ሀገር ከችግርና ከድህነት ስለማትወጣ ወይም ወንጀል ሰራሽ ተብላ ብትጠየቅ የሌላ ሀገር ዜግነቷ ያስጥለኛል ብላ ነው፡፡

አስገራሚው ነገር ግን ንግስት ነኝ የምትለው ልቧን ብሯን ዜግነቷን ሌላ ቦታ አስቀምጣ ባዶ እጇን ወደ መጣችባት ሀገር መቶ ሚሊዮን ህዝብ ጠቅልዬ እገዛለሁ ብላ መመኘቷ ይገርማል፡፡ ሴትየዋ አሁን በህግ ቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ የሰው ሀገር ዜጋ እንዲህ በጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድ ገብቶ የሀገር ሰላም ሲያውክ ዝም ብሎ ማየቱ ቢያስጠይቅም ዘግይቶ ፖሊስ የደረሰበት አቋም ጥሩ ነው፡፡

ይሄ ጠበል አለኝ የሚለው፣ ከኔ ወዲያ ብሎ የሚንጫጫው ወይም ካልፈወስኳችሁ እያለ በየቀኑ የሀሰት ትንቢት የሚዘራው ተቋም አልባ ነጋዴ ሁሉ ፓስፖርቱ ቢታይ ለክፉ ቀን ብሎ የሸሸገው የሳውዲ፣ ወይ የአሜሪካ ወይ የአውሮፓ ዜግነት ይዞ ይሆናል፡፡ ከንግስት ነኝ ባይዋ የምንረዳው በራችንም ልባችንም ክፍት መሆኑን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ እንኳን ቢያንስ በራችንን እንዝጋ፤

Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top