Connect with us

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእቅዴ መሰረትም ሀምሌ 4 ተማሪዎቼን አስመርቃለሁ አለ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት መስጠቴን ቀጥያለሁ ፥ በእቅዴ መሰረትም ሀምሌ 4 ተማሪዎቼን አስመርቃለሁ አለ
Photo Facebook

ወንጀል ነክ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእቅዴ መሰረትም ሀምሌ 4 ተማሪዎቼን አስመርቃለሁ አለ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት መስጠቴን ቀጥያለሁ ፥ በእቅዴ መሰረትም ሀምሌ 4 ተማሪዎቼን አስመርቃለሁ አለ

በኮቪድ 19 ምክንያት ተማሪዎቹን ወደየቤታቸው የሸኘው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ተጠቅሜ የምሰጠው ትምህርት በጥሩ ሁኔታ ቀጥሏል አለ፡፡

ተማሪዎቹን በያሉበት ሆነው የምርቃት መርሀ ግብራቸው እንደሚካሄድም አሳውቋል፡፡ዩኒቨርሲቲው ለቅድመ መደበኛ እና ድህረ መደበኛ ተማሪዎች የሁለተኛ ሴሚስተር ትምህርትን በኢሜል ፥ በድረ ገጽ እና ሌሎች መንገዶችን እየሰጠ እንደሆነ ያሳወቀ ሲሆን የዘንድሮ ተመራቂዎችም የመመረቂያ ጽሁፋቸውን በቪዲዮ ታግዘው ካሉበት ሆነው እንደሚያቀርቡ ገልጿል፡፡

ጎግል ሀንግ አውት እና ማይክሮሶፍት ሚት ለዚህ አገልግሎት እንደሚጠቀምም አሳውቋል፡፡የምርቃት መርሀ ግብሩም በተመሳሳይ የመገናኛ ዘጼዎች ታግዞ እና በመገናኛ ብዙሃን እየተላለፈ ሀምሌ 4 ቀም እንደሚካሄድ ዩኒቨርሲቲው ይፋ አድርጓል፡፡

(አዲስ ልሳን ጋዜጣ)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top