Connect with us

አዲስ አበባን በትኩረት ማየት ግድ ይላል!!

አዲስ አበባን በትኩረት ማየት ግድ ይላል!!
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

አዲስ አበባን በትኩረት ማየት ግድ ይላል!!

አዲስ አበባን በትኩረት ማየት ግድ ይላል!!

(ንጉሥ ወዳጅነው – ድሬቲዩብ )

አመፀኝን በህግ ማስከበር ስርአቱ ከመዳኘትና የአገር ደህንነትን ከማረጋጋጥ ጎን ለጎን ስለመኖሪያችንና የጋራ ከተማችን አዲስ አባባ መነጋጋር የዛሬው ምርጫዬ ነው፡፡ በተለይም በመዲናዋ መልካም አስተዳዳርና ፍትሃዊነት ያለሉበትን ደረጃ መፈተሸን ማስታወስ ይበጃልና !!

ከዓመታት  በፊት  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (6ኪሎ) ሬጅስትራር ጽ/ቤት ግድግዳ ላይ በተንጠለጠለ የማስታወቂያ ሰሌዳ ውስጥ ከተካተቱት ጽሑፎች አንዷ ቀልቤን ስባው ስለነበር በማስታወሻዬ ላይ አስፍሬያታለሁ ፡፡ እንዲህ ትላለች ‹‹Yesterday’s method may not be fit to solve today’s problem, there fore change for the better›› ወደ አማርኛ ግጥም ስንለውጣት፡-

‹‹የትናንቱ ዘዴ የዛሬውን ችግር ሊፈታ ካልቻለ

የተሻለ ለውጥ ለተሻለ ውጤት ቢፈለግ ምን አለ?››

እንደማለት ናት፡፡ ቁም ነገሩ ያለው የተሻለ ለውጥ (Change for the better) የሚለው ላይ ነው ፡፡  

ዛሬ ከአገራችን አልፋ ለአፍሪካ ህብረት መቀመጫና ለዓለም የዲፕሎማቲክ ከተማነት የበቃችዉ አዲስ አበባ ከ137 ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረች ነች ፡፡ በዉስጧም በግርድፍ ግምት እስከ 5 ሚሊዮን ህዝብ የሚደርስ ነዋሪ የያዘች ሲሆን፤ ከሞላ ጎደል ከመላዉ የአገሪቱ አካባቢዎች በታሪክ አጋጣሚ የተሰባሰቡ ዜጎችን እንዳቀፈች ይታመናል ፡፡ ግን አሁንም ነዋሪዎቿን በፍትሃዊነትና በእኩልነትነት የምታስተዳዳርበት ጥብቅ ስረአት ያስፈልጋታል ፡፡

 የአንድ አገር የጋራ ከተማና  ዋና መዲና በሚመራበትና በሚተዳዳርበት መንፈስ የአገሪቱ ዜጎች በፍትሃዊነትና በጋራ ቤትነት መርህ እንዲጠቀሙበት የማድረጉ ስራ ለነገ ሊባል የሚችል አይደለም ፡፡ ኢፍትሃዊነትንም ሆነ ፀረ እኩልነት ድርጊትን መልሶ በሌላኢፍትሃዊነት ማረም ስለማይቻል ብቃት፣ እውቀተ፣ ተወዳዳሪነትና መደጋጋፍን መሰረት ያደረገ የሰው ሃይል ምደባና ስምሪት ነው መቅደም ያለበት ፡፡ እንጅ የአንድ ብሄር ወይም ቡድን አስተሳሳብን ከጫፍ ጫፍ ለማንበር መሞከር ትክክል ሊሆን አይችልም ፡፡ በፍፁም !!

አዲስ አባባ ለረጅም ዘመናት የአገሪቱ ማዕከላዊ መንግስት ሀብት ፣እዉቀትና ቴክኖሎጂ የፈሰሰባትን ምድር ናት፡፡ በዉስጧ ያሉ ህዝቦች ከራሷ አልፈዉ ፣ ከሌላውም  ዓለም ለዘመናት ሰርተዉ ለልጅ ልጅ እያስተላለፉ የቆዩና በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ ሰርተውና ተቀይረው በመዲናዋ የፖለቲካና ኢኮኖሚ የስበት ማእከልነት እየተሳቡ በልፅገው ያበለፀጎት መሆኑም ሊካድ አይችልም ፡፡

 በዚህ የዘመናዊነት ጉዞ ውስጥ በማንነቱ የተሰባጠረና ውህድ ማንነት (ኢትዮጵያዊነት) ያለው ህዝብ የተፈጠረ ሲሆን፣ በንቃተ ህሊናውም ሆነ በአገር ፍቅሩ ሲመዘን አብዛኛው ነዋሪው በብሄር ፓለቲካ የሚነዳ እንዳይሆን ሆኗል ፡፡ ያም ሆኖ ግን በአርሶ አደሩና በከተሜው ፣ወይም አገዛዞች ላይ በሚጣበቀው ጥገኛ ኢሊትና በለፍቶ አደሩ ወይም ካሳለፍነው 30 አመታት አኳያ ደግሞ በዘውግ ፖለቲካው እየተቧደነ የሚመዘብረውና ብዙሃኑ ህዝብ ኢፍትሃዊ የምጣኔ ሀብት ገፅታ ሊታይባቸው ችሏል ፡፡

ይህን በቀላሉ ለማየት ከተማዉ መኖሪያዎቿ ከደሃ ጉሮኖዎች እስከ ታላላቅ ቪላና ግዙፍ ህንፃዎች ድረስ አይነታቸው መብዛቱ አንድ ምልክት ነው፡፡ ነዋሪዎቿም  ከምስኪኗ ቅጠል ተሸካሚ “የኔቢጤ” አንስቶ በዘመናዊ አውቶሞቢል እስከሚንፈላሰሰው ድረስ…፣ በቀን አንድ ብር ለማግኘት ከሚቸገረው ድሃ አንስቶ በሳምንት የሚሊዮኖዎች ብር እቁብ እስከሚጥለው ባለፀጋ የሞሉባት ናት ፡፡ ለኢፍትሃዊ ገጽታዉ መባባስም ሙስናና የስርዓቱ ብልሽት አስተዋፅኦ አላደረገም ማለት አይቻልም ፡፡

በተለይ መዲናዋን ለዘመናት ያስቸገራትን ብልሹ አሠራርና የጥገኝነት ፖለቲካ ኢኮኖሚን ለመቅረፍ ህዝቡን ከዳር ዳር ባሳተፈ መንገድ ሳይታገሱ መታገል ከወዲሁ መጀመር አለበት ፡፡ በዚህ ረገድ የነባሩ አስተዳዳርና ምክር ቤት ስህተትን ላለመድገም መትጋት ብቻ ሳይሆን፣በመደራደር ፣በሙስናና በእከክልኝ ልከክልህ የደነደነውን የመሬት ፣የገቢ፣የግዥና ሽያጭ፣ የብቃትና ፍቃድ ሰጭ አካላት መዋቅር …. መገለባባጥ ያስፈልጋል፡፡

በመሰረቱ በመዲናዋ ከለዉጥ በኋላም ባልጠራ ምዘናና በለዉጥ ሃይል ስም በርካታ ችግር ያለባቸዉ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ቆዳቸዉን ገልብጠዉ እንደተሰገሰጉ ይታወቃል ፡፡ በከተማዉ  አስተዳደር ውስጥ ከዋናው መስሪያ ቤት (ማዘጋጃ) ጀምሮ በየክፍለ-ከተሞች በኩል ቁልቁል ወረዳ  ድረስ ብዙ የሠራተኛና የሃላፊ  ጉድ ሊመዘዝ ይችላል ፡፡ ጠንካራ የግምገማ ስረአትና በወቅታዊ አንገብጋቢ ጉዳች መነዳቱ የፈጠረው መዘናጋትም ጥገኝነቱን አፋፍቶታል ፡፡

የአብዛኛው አመራር ስራ የመዲናዋን ፀጥታና ሰላም ማስጠበቅ፣በመዲናዋ ኢፍትሃዊነት እንዳይንሰራፋ ማድረግ ፣መልካም አስተዳዳርና የህግ የበላይ እንዲረጋጋጥ መረባረብ ፣ድህነትና የሥራ አጥነት ችግሮች እንዲቀረፉ መትጋት ላይ የሚያተኩር  ነው፡፡ እነዚህን ብርቱ ተግባራት ደግሞ ሳይቀናጁና በቁርጠኝነት ሳይሰሩ ብቻ ሳይሆን ፣ዘርና ሰፈር ወይም አመለካካትና እምነት እያዩ ለማቃለል መሞከር ከቶም ጠብ የሚል ነገር ሊኖር አይችልም ፡፡እናም ትኩረት ለአዲስ አባባ የማያቋርጥ ለውጥ ይሰጥእንላለን !!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top