Connect with us

አርቲስት ንብረት ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሮናቫይረስ እንዲከላከል ቅስቀሳ አደረገ

አርቲስት ንብረት ገላው ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሮናቫይረስ እንዲከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ቅስቀሳ አደረገ
Photo: Social media

ዜና

አርቲስት ንብረት ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሮናቫይረስ እንዲከላከል ቅስቀሳ አደረገ

አርቲስት ንብረት ገላው ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዲከላከል የግንዛቤ በመገናኛና ገርጂ አካባቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ቅስቀሳ አደረገ።

አርቲስቱ ህብረተሰቡ ራሱን ከቫይረሱ ቫይረስ እንዲጠብቅ የጥንቃቄ መልዕክቶችን አስተላልፏል።

በቅስቀሳውም ህብረተሰቡ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ የእጁን ንጽህና በአግባቡ እንዲጠብቅና አካላዊ ርቀቱን ጠብቆ መንቀሳቀስ እንደሚገባው አስገንዝቧል።

መዘናጋት ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን በማንሳት ቀላልና እጅግ ጠቃሚ የሆኑትን የመከላከያ ዘዴዎች ህብረተሰቡ ሳይዘናጋ እንዲፈጽም ጥሪ አቅርቧል።

አርቲስቱ ”ቅስቀሳውን እያደረኩ ያለሁት የዜግነት ግዴታየን ለመወጣት ነው” ሲል ተናግሯል።

ኢትዮጵያ ያላት የኢኮኖሚ አቅም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ጉዳት የመቋቋም አቅሟን የሚፈትን በመሆኑ ችግሩን አስቀድሞ ለመከላከል ህብረተሰቡ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መክሯል።

በኢኮኖሚ ያደጉ አገሮች ላይ እየደረሰ ካለው ጫና መማር እንደሚያስፈልግም ገልጿል።

ህብረተሰቡ መንግስት የሚያስተላልፋቸውን መመሪያዎች በመተግበር አገሩን ሊታደግ እንደሚገባ አርቲስት ንብረት ገልጿል።

”ማንኛውም ዜጋ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የበኩሉን ሚና መጫወት አለበት” ሲል መዕልክቱን አስተላልፏል።

የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ለማስቻል የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የማይናቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል።

ምንጭ:- ኢዜአ

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top