Connect with us

ፈጣሪ ኾይ እኛን ተወን፤ እንዲህ ዓለምን ጭምር በጥልቀት ስለተደረዱ አባቶቻችን ብለህ ማረን

Photo: Social media

ባህልና ታሪክ

ፈጣሪ ኾይ እኛን ተወን፤ እንዲህ ዓለምን ጭምር በጥልቀት ስለተደረዱ አባቶቻችን ብለህ ማረን

ፈጣሪ ኾይ እኛን ተወን፤ እንዲህ ዓለምን ጭምር በጥልቀት ስለተደረዱ አባቶቻችን ብለህ ማረን፤ የቀዳሚ ሙፍቲ ዱዓ-ዓለም ሰምቶት ቢኾን እንደ ክትባት በቆጠረው ነበር፡፡
****
ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

የራሳችንን አባቶች መች መሰልን? ዘፋኙን ለመመስል የደከምንው፤ ኳስ ተጫዋቹን ለመኾን የለፋነው፤ ሳይንቲስቱ ያለውን ለማመን የተጣደፍነው አወቅን ብለን ነበር፤ እውቀት ከፍርሃት አላወጣንም፡፡ ሁሉን ድል ማድረግ ጨረቃ ላይ ኾኖ ፎቶ ማንሳት ብቻ የመሰላት ዓለም አጠገቧ ባለ ችግር መቃብር ወረደች፡፡ ዓለምን የሚያስተምሩ አባቶች ትናንት ነበሩን ዛሬም አሉን፤

በእኚህ ታላቅ ዓሊም አሻግሬ የበቁ አባቶቻችንን አየሁ፡፡ የገዳማውያኑን ልብ የዓሊሞችን መንፈስ ተረዳሁ፡፡ እኛ ሞት አፋፍ ላይ ሆነን በአሟሟት አቃቂር ተወጥረናል፡፡ እኛ ከመታዘዝ እንቢ ማለት የመዳን መንገድ ነው ብለናል፡፡ እኛ ትልቁን አዋርደን ከፍ ማለት የምንፈልግ የትንሽ ሀሳብ ተገዢዎች ነን፡፡ ግን አምናለሁ እንዲህ ስላሉት አባቶች ብሎ ምድራችንን ይምራል፡፡

የቀዳሚ ሙፍቲውን ንግግር ዓለም በየቋንቋዋ ሰምታው ቢኾን ምንኛ ደግ ነበር፡፡ ትውልድ ራሱን የሚያይበት መስታወት መኾኑን ቢያምን ችግርን እንደምን እናመልጠው ነበር፡፡ ይህ የክትባት ያክል ከጫፍ ጫፍ የሚያድን መልእክት ነው፡፡

እውነት ነው፤ ሙስሊሞች ነን ብለን ሁለት ጎራ ተቧድነን መስጂዶች የግጭት አውድ አልሆኑም፤ ፖለቲካ ነድቶን ሁለት ሲኖዲዮስ ይዘን አልኖርንም፤ ዛሬስ ዘርና ፖለቲካ ከትናንት አላስተምር ብሎን በእምነት ስም ሸፍጥ አልሰራንም፡፡ ለምን ከመስጂድና ከቤተ ክርስቲያን አስወጣን የሚለውን ለመመለስ እኮ እያንዳንዱ ሰው በቂ ነበር፤ ይኽ ጥያቄ መች እግዜር ዘንድስ የሚቀርብ ነበር፡፡

እኛ ግን ጥቂት አባቶች አሉን፤ ስለተሰወሩና ዓለምን ስለናቁ አባቶቻችን ሲል የጥፋት ሁሉ ክንድ ጉልበቱን ይቀንሳል፡፡
ቀዳሚ ሙፍቲ ዓለምን ጭምር መክረዋል፡፡ ሰው ምን ገጥሞት አለመማሩን አሳይተዋል፡፡ ከሱናሚ በኋላ እነኛ የመዝናኛ ዳርቻዎች ዛሬም የሰዶማውያን የጫጉላ ሽርሽር ቦታ አይደሉም? ስመ ብዙ ከኾኑት የማዕበል ንፋሶች በተረፍን ማግስት ዓለም ወደ ቀደመ ትምክህቷ አልገባችም? ግን ጉልበቷን አየችው፤ እውቀቷን አየችው፤ ጥበቧን አየችው፤ ሞትና ፍርሃት ሁሉን ድል ነሱ፡፡

የሰለጠኑቱ ሀገራት እምነት በቃ ብለው አብያተ ክርስቲያናትን ጭፈራ ቤት አላደረጉም፤ ፈጣሪ የለም ብለው አልተመጻደቁም፡፡ እነሱን ለመመስል በመፈለጋችንና በመሞከራችን የእነሱን ኩርኩም ቅንጣቷን ስንቀምስ ግን መግቢያ አጣን፡፡

እኔ አሜን ካልነው ዋናው እንመለስ የሚለው ነው፡፡ እንመለስና ከፈጣሪ እንዋቀስ ስትመለሱ ፊቴን እመልሳለሁ ብሏልና፤ ያኔ ምንው ምን ብለህን ነበር እንበል፤ ኑ እንመለስ፡፡ ከጥላቻ፣ ከግጭት፣ ከሆዳምነት፣ ዓለምን አብልጦ ወዶ ፈጣሪን ከመራቅ እንመለስ፤ አሁን እንንቃ ሳይሆን እንመከር፤ ምክርን እንቀበል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top