Connect with us

በአዲስ አበባ በህዝብ ትራንስፖርት የአገልግሎት መስጫ ሰዓት ላይ ማሻሻያ ተደረገ

በአዲስ አበባ በህዝብ ትራንስፖርት የአገልግሎት መስጫ ሰዓት ላይ ማሻሻያ ተደረገ
Photo Facebook

ዜና

በአዲስ አበባ በህዝብ ትራንስፖርት የአገልግሎት መስጫ ሰዓት ላይ ማሻሻያ ተደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በታክሲዎች የአገልግሎት መስጫ ሰዓት ላይ ማሻሻያ መደረጉን አስታወቀ።

በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ በቀጣይ መመሪያ እስከሚሰጥ ድረስ ታክሲም ሆነ ሃይገር አውቶቡስ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት በፊት እና ከምሽቱ 2:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተደርጓል።

በአንጻሩ አንበሳ እና ሸገር አውቶቡሶች በተለመደው የአገልግሎት መስጫ ሰዓታቸው አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆን፥ ታክሲዎችና ሃይገር አውቶቡሶች የመጫን አቅማቸው ወደ መደበኛው እስከሚመለስ ቀደም ሲል የነበረው ታሪፍ በእጥፍ አድጎ ተሳፋሪዎች እንዲከፍሉ ይደረጋል ነው የተባለው።

የአንበሳ እና የሸገር አውቶቡሶች ታሪፍ በነበረበት የሚቀጥል ሆኖ መንግስት በሚያደርገው ድጎማ እንዲሸፈን ይደረጋልም ተብሏል።

ማንኛውም ከተፈቀደው ሰው በላይ ጭኖና ከተፈቀደው ሰዓት ውጭ ሲሰራ የተገኘ ታክሲም ሆነ የሃይገር አውቶቡስ 5 ሺህ ብር የሚቀጣ ሲሆን፥ በተጨማሪም የአሽከርካሪው መንጃ ፈቃድ እስከመጨረሻው እንዲታገድ በማድረግ በሌሎች የሀገሪቱ ህጎች ተጠያቂ የሚደረጉም ይሆናል።

በሃይገር ባስ የተሳፋሪ ቁጥር በወንበር ልኩ በግማሽ ብቻ እንዲጭኑ የተደረገ ሲሆን፥ 14 ሰው ብቻ እንዲጭኑ ውሳኔ መተላለፉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አንበሳ የከተማ አውቶቡስ እና ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አውቶቡሶች 40 ሰው ይጭን የነበረው መደበኛ አውቶቡስ 30 ሰው ብቻ የሚጭን ይሆናል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top