“የኢትዮጵያ አየር መንገድ መደበኛ በረራ በኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ ወደተጠቁ ሀገራት ለጊዜው ማቆም አለበት ስንል” – ዶ/ር አብርሃም ታሪኩ
1. ኮሮና ቫይረስ አደገኛ የሳምባ ምች ሊያመጣ የሚችል እንዲሁም የመተንፈሻ አካል ስራ ማቆም ሊያስከትል መቻሉ!
2. septic shock ወይም ደም ውስጥ የሚሰራጭ ኢንፌክሽን አምጥቶ ኩላሊት ስራ እንዲያቆም አድርጎ ለሞት መዳረጉ
3. ኢንፌክሽኑ ሀገራችን ከተከሰተ ተጠጋግቶ የመኖር ባህላችን አንፃር ለመቆጣጠር በጣም ከባድ ስለሚሆን
4. የሀገራችን የንፅህና ባህል፣የተዳከመ የጤና ስርአት እንዲሁም ከምግብ አለመመጣጠን ጋር ተያይዞ ለስርጭቱ ምቹ ሊሆን ስለሚችል
5. በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚያስፈልጉት የፅኑ ህሙማን መርጃ ክፍሎች (ICU rooms and beds) ፣ መተንፈሻ ማሽኖች (Mechanical ventilators) ፣ አብሮ መደረግ ያለባቸው ምርመራዎች የደም ጋዝ መጠንን (blood gas analysis) ጨምሮ በበቂ ሀገራችን ስለሌሉ በተለይ ደግሞ በሺዎች ለወረርሺኝ ከተፈለገ፤
6. የአለም የጤና ድርጅት የአለም የጤና ስጋት ብዬ ያወጅኩት ደካማ የጤና ስርአት ላላቸው ሀገራት በመስጋት ነው ማለቱ
7. የአለም የጤና ድርጅት ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ውስጥ 12 ከፍተኛ ስጋት (high risk countries) ውስጥ ማስቀመጡ
8. የመንለካው የትኩሳት መጠን ከ14 ቀናት በኋላ ሊከሰት መቻሉ
9. በበረራ ማቋረጥ ምክንያት ልናጣው ከምንችለው ገንዘብ (economy) በላይ በወረርሽኝ ብዙ ሰው ቢሞት ልናጣ የምንችለው በገንዘብ ሲሰላ ስለሚበልጥ (disease burden, disability burden and death burden)
10. ወረርሽኙ ሀገራችን ቢገባ የቱሪዝመም ገቢ፣ ዉጪ የምንልካቸው የእንስሳ ተዋዕፆ ኦና ምግብ ምርቶች ገቢ ሊቆም መቻሉ፤ ሰውም ሌላ ሀገር መዘዋወር መብቱ ሊታገት መቻሉ
11. ወዳጅነቱን ከቻይና ለማስቀጠል የአደጋ መከላከል በረራዎች (evacuation flights) የህክምና እርዳታ በረራዎች (medical rescue and support flights) በጥንቃቄ እንዲቀጥል ማድረግ መቻሉ
12. የህክምና እና የህብረተሰብ ጤና ስነምግባር (ethics) የብዙሃንን ደህንነት ለማሰጠበቅ (isolation) እንደ በሽተኛም ሆነ እንደ ሀገር ስለሚፈቀድ አየር መንገዱ መደበኛ በረራ ለጊዜው ወደተጠቁት ሀገራት ቢያቆም እላለሁ?
ለአሁንም ለወደፊቱም ቢሆን ግን ለንደዚህ አይነት ችግሮች የሚያማክር (scientific committee) ተዋቅሮ በፈጣን ሁኔታ በሳይንስ ተከራክሮ (with scientific debate) ውሳኔ ቢሰጥ እላለሁ! የመቶ ሚሊዮን የጤና አደጋ ባንድ አቅጣጫ በሚያዩ ጥቂት ፖለቲከኞች መወሰን አለበት ብዬ አላምንም። የሐኪሞች ማህበር የት ነው ግን? እኛስ ቢያንስ ያወቅነውን ለማሳወቅ ስለማልን እየጮህን ነው፤ ጆሮ ያለው ይስማ።
#ሐኪም