Connect with us

ሼህ አልአሙዲ ለጫማ ጠራጊው የኢንጅነሪንግ ምሩቅ ወጣት ደረሱለት

ሼህ አልአሙዲ ለጫማ ጠራጊው የኢንጅነሪንግ ምሩቅ ወጣት ደረሱለት
Photo: Facebook

አስገራሚ

ሼህ አልአሙዲ ለጫማ ጠራጊው የኢንጅነሪንግ ምሩቅ ወጣት ደረሱለት

ሼህ አልአሙዲ ለጫማ ጠራጊው የኢንጅነሪንግ ምሩቅ ወጣት ደረሱለት
~ ወጣቱ በቀጣይ ሳምንት በተመረቀበት ሙያ ሥራ ይጀምራል፣

ወጣት ቸኮል መንበሩ ከባህዳር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኬሚካል ምህንድስና የመጀመሪያ ዲግሪውን ቢቀበልም በሙያው ሥራ አግኝቶ አገርና ወገኑን ማገልገል ቀላል አልሆነለትም። ሕይወት ስትፈትነው የዕለት ጉርስ ለመቅመስ የጫማ መጥረግ ሥራ ውስጥ ለመግባት ተገደደ። እናም በባህርዳር ጎዳናዎች ላይ የሰዎችን ጫማ በማሳመር ቀን እስኪያልፍ መታገሉን መረጠ።

የወጣቱን ጥንካሬ ቢቢሲ ከዘገበውና በድሬቲዩብ ለማህበራዊ ድረገፅ አንባቢያ ርዕሰ ጉዳዩ ከተጋራ በኋላ ወጣቱ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆነ።

ኢትዮጵያዊ ኢንጂነር ለጫማ ጠራጊነት ዳግም ተዳረገ...

የሀያ ሰባት አመቱ ቸኮለ መንበሩ እንደማንኛውም ወጣት ኢትዮጵያዊ ኑሮን አሸንፎ ፣ከትልቅ የስኬት ደረጃ ላይ በመድረስ ቤተሰቡን እና አገሩን በመጥቀም ፣በመልካም ስም ያማስጠራት ምኞት ነበረው።

የዚህን ወጣት ልብ የሚነካ ታሪክ የሰሙት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ሊቀመንበር የክብር ዶክተር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ ለወጣቱ ተገቢው ማቋቋሚያ እና በሙያው ሥራ እንዲመቻችለት ያዘዙት ውለው ሳያድሩ ነበር።

ኢትዮ ኤፍኤም 107.8 በትላንትና የማለዳ የበዓል ልዩ ዝግጅት ላይ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኬሚካል ኢንጅነሪንግ ተመርቆ በጫማ ጠራጊነት ህይወቱን ሲመራ ለቆየው ወጣት ቸኮል_መንበሩ ከሼህ ሙሐመድ የገና_ስጦታ እንደተበረከተለት ይፋ አድርጓል።

ከራድዮ ጣቢያው ጋር አጭር ቆይታ ያደረጉት የሆራይዘን ኘላንቴሽን ኢንቨስትመንት ግሩኘ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ “ወጣት ቸኮል ዳግም ወደጫማ መጥረግ አይመለስም። በተማረበት የኬሚካል ኢንጅነሪንግ ሙያ በ ሆራይዘን አዲስ ጎማ ፋብሪካ ሥራ እንዲጀመር ብሎም የመቋቋሚያ ድጋፍ እንዲደረግለት በሼህ ሙሐመድ ተፈቅዷል” ብለዋል። በዚሁ መሠረት ወጣቱ ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ ወደአዲስ አበባ በመምጣት አዲስ ሥራ፣ አዲስ ህይወት እንደሚጀምር አቶ ጀማል አረጋግጠዋል።

እንደማንኛውም ነጋዴ ትርፍ ከማስላት ይልቅ የወገናቸውን ችግር መፍታት ቅድሚያ የሚሰጡት የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ ከስድስት ወራት በፊት የአዲስአበባ ከተማን የዳቦ እጥረት እና የዋጋ ንረት ለመቅረፍ የሚረዳና በሰዓት 80ሺ የዳቦ ምርት የሚያቀርብ ሸገር የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ እንዲገነባ በፈቀዱት መሠረት በአሁኑ ወቅት ግንባታው ከ90 በመቶ በላይ መጠናቀቁና ቀሪውን ሥራ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ መገለፁ የሚታወስ ነው።

በተመሳሳይ መልኩ የገቢ ምርትን በአገር ውስጥ ምርት ለመተካትና የውጭ ምንዛሪ በማዳን የአገር ኢኮኖሚን የመደገፍ ዓላማ ያለው ግዙፍ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ለመገንባት በያዝነው ወር መጀመሪያ በአዲስአበባ ከተማ የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል የሆነውም በለጋሱ፣ በድሆች አባት የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ውሣኔ መሆኑም አይዘነጋም።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top