Connect with us

የተመድ አካባቢ ጥበቃ የጠ/ሚ ዐብይን የሰላም የኖቤል ሽልማት አወደሰ

የተመድ አካባቢ ጥበቃ የጠ/ሚ ዐብይን የሰላም የኖቤል ሽልማት አወደሰ
Photo: Facebook

አለም አቀፍ

የተመድ አካባቢ ጥበቃ የጠ/ሚ ዐብይን የሰላም የኖቤል ሽልማት አወደሰ

የተመድ አካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም (UNEP) ህዳር 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ባደረገው ወርሃዊ የቋሚ ተወካዮች ጉባኤ (CPR) ስብሰባ ወቅት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የሰላም የኖቤል ሽልማታቸውን በመቀበላቸው መደሰቱን ገልጿል።

በኬንያ የተመድ ጽ/ቤት የአውሮፓ ህብረት፣ የብራዚል፣ የኮሎምቢያ እና ሌሎችም ተወካዮች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማታቸውን በመቀበላቸው የተሰማቸውን ደስታ የሚገልጽ ንግግር አድርገዋል።

በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው የኖቤል ሽልማቱን እንደቀላል አንወስደውም ብለዋል። ሽልማቱ ለኢትዮጵያ የተሰጠ እውቅና ብቻ ሳይሆነን ኃላፊትም ጭምር መሆኑን ጠቅሰው ሀገራችን ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከምንጊዜውም በላይ አበክራ እንድተሰራ የሚያተጋት ነው ብለዋል።

አምባሳደሩ ፤ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የኖቤል ሽልማታቸውን በመቀበላቸው ደስታቸውን የገለጹና ድጋፋቸውን ያሳዩ የተለያዩ ሀገራትና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮችን አመስግነዋል።

(ምንጭ፡-በኬንያ የኢት. ኤምባሲ)

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top