Connect with us

ጠ/ሚ ዐብይ በትግራይ ተፈፅሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ ፈቀዱ

ጠ/ሚ ዐብይ በትግራይ ተፈፅሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ ፈቀዱ
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

ጠ/ሚ ዐብይ በትግራይ ተፈፅሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ ፈቀዱ

ጠ/ሚ ዐብይ በትግራይ ተፈፅሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲጣራ ፈቀዱ

በትግራይ ክልል ተፈፅሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የአፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በመሆን እንዲያጣራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪውን ያቀረቡት በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ እና ዳራው ላይ ለአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ባቀረቡት መግለጫ ነው፡፡

በትግራይ ክልል በዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈፅመዋል የሚለው ክስ መሰረተ ቢስ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አክሱምን ጨምሮ በክልሉ ተፈፅሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማጣራት ገለልተኛ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

የሚመለከታቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማትም በምርመራው ላይ እንዲሳተፉ መንግሥት ፈቃደኝነት ማሳየቱንም አስታውሰዋል፡፡

በቀጣይም የአፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በክልሉ ተፈፅሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከኢሰመኮ ጋር በመሆን እንዲያጣራ የመንግሥት ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር እርምጃ የወሰደችው በራሷ ግዛት ውስጥ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስምረውበታል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት እና አባል ሀገራቱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለኢትዮጵያ ላሳዩት አጋርነት እና ላበረከቱት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡(ኢቢሲ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top