Connect with us

ጠ/ሚ ዐብይ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ

ጠ/ሚ ዐብይ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ
አብመድ

ዜና

ጠ/ሚ ዐብይ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ

ጠ/ሚ ዐብይ የኤርትራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ

~ ሁለቱ ሀገራት በድንበር አካባቢ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማስጀመር ተስማምተዋል፣

 ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በድንበር አካባቢ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ዳግም ለማስጀመር መስማማታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ተናገሩ፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ስምምነት ደርሰዋል።

ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ ወደ አስመራ ሮኬቶችን በማስወንጨፉ የኤርትራ ሰራዊት ወደ ድንበር እንዲገባ እንዳደረገው ገልጸዋል።

መሪዎቹ በውይይታቸው ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ ወደ አስመራ ሮኬቶችን በማስወንጨፉ ወደ ድንበር ገብቶ የነበረው የኤርትራ ጦር ከድንበር ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አካባቢውን እንዲቆጣጠር ተስማምተዋል ።

በድንበር አካባቢ በሁለቱ ሀገራት መካከል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ለማስጀመር ስምምነት ላይ ደርሰዋልም ነው ያሉት፡፡

ሀገራቱን በልማት ለማስተሳሰር የተጀመሩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ለመጀመር እንደተስማሙ መገለጹን ፋብኮ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኤርትራ ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት አጠናቀው ተመልሰዋል፡፡(አብመድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top