Connect with us

“ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት እሷን ማጥፋት ኢትዮጵያን ማጥፋት ነው” – አትሌት ሀይሌ ገ/ሥላሴ

"ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት እሷን ማጥፋት ኢትዮጵያን ማጥፋት ነው" - አትሌት ሺ አለቃ ሀይሌ
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

“ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት እሷን ማጥፋት ኢትዮጵያን ማጥፋት ነው” – አትሌት ሀይሌ ገ/ሥላሴ

“እኔ ዓለምን በኦሎምፒክ ስዞር ኪዳነ ምህረትን በልቤ ይዤ ነው ለዚህም ሁለት የሜዳሊያ ሽልማቶቼን ለእንጦጦ ኪዳነምህረት ሰጥቻለው።”

“ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀገር ናት እሷን ማጥፋት ኢትዮጵያን ማጥፋት ነው”

ቤተክርስቲያን ሁሌም ፈተና ይበዛባታል እኔን ጨምሮ በክርስቲያኖች ላይ የደረሰው የንብረት መውደም መከራና ጭፍጨፋ የእናቶችን ስቃይ ሳይ የእኔን ንብረት ቃጠሎ እረሳውት የዕዮብንም ታሪክ አስታወስኩ። አዘንኩም! እኔ ኢትዮጵያ ሀገሬን ከልቤ የምወድ ሰው ነኝ።

በሀይማኖቴም እምኮራ ኦርቶዶክስ ነኝ። ይህን ሁሉ መከራ ቤተክርስቲያን ቢደርስባትም ወደ እግዚአብሔር ከመፀለይ ውጭ ቂም በቀል አፀፋ ለመስጠት እምትነሳ አይደለችም። ክርስቲያን በመከራ ውስጥ ነው እሚያልፈው።

እግዚአብሔር ሰጠኝ እግዚአብሔር ነሳ ለጠላቶቻችን ልቦና ይስጥልን በቀል የእግዚአብሔር ነው።

እኔ ዓለምን በኦሎምፒክ ስዞር ኪዳነ ምህረትን በልቤ ይዤ ነው ለዚህም ሁለት የሜዳሊያ ሽልማቶቼን ለእንጦጦ ኪዳነምህረት ሰጥቻለው።

በተቀደሰው ስርዓት በተክሊልም ያገባውባት ቤተክርስቲያን ናት እንጦጦ ኪዳነምህረት።
እኔ ብዙ የበጎ ስራ መልካም ነገሮችን ባደርግም እሄን አደረኩ ብዬ መናገር አልወድም ያደረኩለት ሰው ይናገር እንጂ የተሰጠኝን በመስጠቴ ውዳሴ ከንቱን አልፈልግም።

አትሌት ሺ አለቃ ሀይሌ ገብረሥላሴ በማህበረ ቅዱሳን ቲቪ የአዲስ ዓመት ልዩ እንግዳ ከተናገረው የተቀነጨበ!
Via ጨለሚት ኪዳነምህረት ገዳም

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top