Connect with us

ኦርቶዶክስ ሀገር ናት ብሎ ሃይማኖትነቷን መንፈግ

ኦርቶዶክስ ሀገር ናት ብሎ ሃይማኖትነቷን መንፈግ
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

ኦርቶዶክስ ሀገር ናት ብሎ ሃይማኖትነቷን መንፈግ

ኦርቶዶክስ ሀገር ናት ብሎ ሃይማኖትነቷን መንፈግ፤
በዓለም የትም በነጻነት የምታከብራቸው ጥምቀትና መስቀል ለነጻነቷ በወደቀችላት ሀገር ግን የንትርክ ምክንያት ነው፡፡
****
ከስናፍቅሽ አዲስ

ኦርቶዶክስ ሀገር ናት የዘመኑ ፖለቲከኞች አፍ መፍቻ ቋንቋ ናት፡፡ መነሻቸው ምእመኑ እምነቱ ሀገር እንደሆነች፤ ለሀገር መሰደዷን ለሀገር መቃጠሏን፣ ሀገር ማኖሯን፣ ለሀገር መታረዷን ስለሚያምን ያለው ነው፡፡ ያለውን ብለህው ልቡ ግባ የዚህ ዘመን አራዳ ፖለቲከኞች ብሂል ናት፡፡ እናም በየአደባባዮ ኦርቶዶክስ ሀገር ናት ይሏታል፡፡

ኦርቶዶክስ ሀገር ናት ብለው በሀገሯ በነጻ ማምለክን ነፍገዋታል፡፡ ብሔርም ፖለቲካም የጠቡ ፍጻሜ የኦርቶዶክስ ቤተ እምነትን ማንደድ ነው፡፡ ግራህን ለመታህ ቀኝህን ስጥ የሚለው አስተምሮት መሰረቴ ነው የምትለው እምነት ለዚህ ህግ አልባ ሥርዓት ተጋለጠች፡፡

የመስቀል በዓል አከባበርን ስለማክበር ዛሬም ኦርቶዶክሳውያን በሀገራቸው የዱባይን ያህል መብት የላቸውም፡፡ ኢስላማዊ የአረብ ሀገራት እንኳን የደመራውን ውበት አላደበዘዙትም፡፡ እምነት አልባዎቹ ኮሚውኒስት ሀገራት እንኳን ለጥቂት ኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክሳውያን መከራ አልሆኑባቸውም፡፡ ዛሬም ግን በኢትዮጵያ ማንም እየተነሳ የግል ደባውን በስልጣን ስም ኦርቶዶክሳዊቷን እምነት ለመበደል ሲጠቀምበት ማየት ያሳዝናል፡፡

እስከ መቼ የሁሉም ጥያቄ ቢሆንም ጥምቀትና መስቀል በመጡ ቁጥር የታቦት ማደሪያና የደመራ ስፍራ ለማግኘት ልመናው፤ ሥርዓቱን ለማከናወን በየዓመቱ የሚቀያየረው ከንቲባ ደጅ ጥናት ብቻ ስቃዮ ብዙ ነው፡፡ አምና የከለከለው ከንቲባ በቀጣዮ አመት ስለሚባረር ደግሞ አዲሱ ከንቲባ እንደ አምናው እምነት ማፈን ብቻ ተልእኮው መስሎት አንድ ታሪክ ሰርቶ የሚያልፈው ኦርቶዶክሳውያኑ እንዲህ ባለው ሥርዓት ደስተኛ እንዳይሆኑ ማድረግ ነው፡፡

የእምነት ነጻነት እርግጥ በኢትዮጵያ ብዙ ችግሮች አሉበት፤ ብሔርን ካባ ያደረጉ እምነቶች አሉ፤ እምነቶችም እንደ ፌዴራሊዝሙ ሥርዓት እንዳሻቸው የሚሆኑበት የየራሳቸው ቀጠና አላቸው፡፡ በሀገራቸው አንዱ እምነት አንዱ ስፍራ ንጉሥ ሌላው ስፍራ ጭሰኛ ሲሆን የምንመለከተው በመንግስት አለመሰልጠን ነው፡፡ በዚህ አመት የደመራ በዓል አከባበር ላይ ልዩነት የተፈጠረባቸው አካባቢዎች ምክንያትም እንዲህ ያለው የባለ ግዛት ነኝ ጉልበት ዛሬም ከመከራ ያልወጣችው ኦርቶዶክስ ላይ አርፎ ነው፡፡ ጥያቄያችን ይሄ መቼ ያቆም ይሆን ነው?

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top