Connect with us

የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት እርዳታው ሊታገድ እንደማይገባ ጠየቁ

የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት እርዳታው ሊታገድ እንደማይገባ ጠየቁ
Photo: Social Media

አለም አቀፍ

የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት እርዳታው ሊታገድ እንደማይገባ ጠየቁ

የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት እርዳታው ሊታገድ እንደማይገባ ጠየቁ

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ስትሰጠው የነበረው እርዳታ ሊታገድ እንደማይገባ ስድስት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያቤት በላኩት ደበዳቤ ጠየቁ።

የኮንግረስ አባላቱ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በጻፉት የተቃውሞ ደብዳቤ እንደገለጹት ኢትዮያውያን በራሳቸው ባለሙያዎችና በራሳቸው ገንዘብ እያሰሩት መሆኑን ገልጸውላቸዋል።

የታላቁ የኢትዮያ ህዳሴ ግድብ ለአመታት ሲመኙት የነበረው የተፈጥሮ ሃብታቸውን ተጠቅመው ከድህነት የመውጫ መንገዳቸው ብሎም የብሄራዊ ኩራታቸው ምንጭ ነው ብለዋል በደብዳቤያቸው።

ከግማሽ ሚሊየን የሚበልጡ ዳያስፖራዎች በአሜሪካ እየኖሩና የሁለቱ ሃገራተ ግንኙነትም ከአንድ መቶ አመታት የተሻገረ ስለመሆኑ ያነሱት የኮንግረስ አባላቱ በጤና አጠባበቅና በምግብ ዋስትና ላይ በሚያተኩረው ሰብአዊ እርዳታዎች ላይ አሜሪካ ያደረገችው የድጋፍ ማቋረጥ እርምጃ በቀጠናው የአሜሪካ ታማኝ አጋር ለሆነችው ኢትዮጵያ ያልተጠበቀ ውሳኔ ነው ብለውታል።

በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልእኮ ፣አልሸባብን በመዋጋት ሁነኛ የአሜሪካ አጋር በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ የተደረገው የእርዳታ ማቋረጥ በአሜሪካ ብሄራዊ ጥቅሞች ላይ ተቃራኒ ውጤት ሊያስከትል ከመቻሉም በላይ ለመቶ አመታት የዘለቀውን የሃገራቱን ጠንካራ ግንኙነት ሊያበላሸው ይችላል ብለዋል።

ወንዙን በሚመለከት የታችኞቹ የተፋሰሱ ሃገራትን ስጋትና የጉዳዩን ውስብስብነት እንደሚገነዘቡ ያስረዱት የኮንግረስ አባላቱ የአሜሪካ አስተዳደር ግልጽ ወገንተኝነት ይዞ ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ ለማቋረጥ መወሰኑ አሜሪካ የነበራትን ገለልተኛ የአደራዳሪነት ሚና ከማበላሸቱ በተጨማሪ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የተጋፋና የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪዎችን ጥረት ዋጋ ያሳጣ ስለመሆኑም አንስተዋል።

አሜሪካ የገለልተኛ አደራዳሪነት ሚናዋን በማስቀጠልና ለጉዳዩ አስማሚ መፍትሄ እንዲገኝ እንደምትሰራ ያላቸውን እምነት በገለጹበት ደብዳቤያቸው ያገደችውን እርዳታ ለኢትዮጵያ በመልቀቅ በገለልተኛ የአደራዳሪነት ሚናዋን እንድትቀጥል ጠይቀዋል።

#ena

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top