Connect with us

የህዳሴ ግድብ ድርድርና የአሜሪካ የዲፕሎማሲ ውድቀት

የህዳሴ ግድብ ድርድርና የአሜሪካ የዲፕሎማሲ ውድቀት
Photo: United World International

ትንታኔ

የህዳሴ ግድብ ድርድርና የአሜሪካ የዲፕሎማሲ ውድቀት

“አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ቀጥተኛ ጫና ከመፍጠር በዘለለ የጋራ መግባባት ላይ እንዲደረስ የሚያስችል አንዲትም አበርክቶ እንዳላስገኘች ልብ ሊባል የሚገባ ጉዳይ ነው” ::

ይህን ያለው በአለማቀፍ ምሁራን የተሠናዱ የጂኦ ፓለቲካ ትንታኔዎችን ነሚያቀርበው United World International የተባለው ተቋም ነው።

ተቋሙ UWI “The Gerd Issue: a US diplomatic Defeat” ሲል ዛሬ ባስነበበው ትንታኔው እንደገለፀው “በዓመቱ መጀመሪያ ግብፅ ፍላጎቷን ለማሳካት የአሜሪካን ርዳታ በመሻት ድርድሩን አሜሪካ እንድትገባበት ጠየቀች። ነገር ግን ትራምፕ የተባለውን መፈፀም አልቻሉም፡፡ ኢትዮጵያም ከድርድሩ ወጣች” ብሏል።

ጥንቃቄን በሚሻው በዚህ የዲፕሎማሲ ጉዳይ ላይ ዋሽንግተን አዲስ አበባ ላይ ቀጥተኛ ጫና ማድረግን መረጠች። ሆኖም አፍሪካዊት ሀገር ኢትዮጵያ ለአሜሪካ ጫና አላጎነብስም ማለትን መረጠች። ይልቁንም የራሷን ጥቅም አስቀደመች። ይህ ክስተት ለዶናልድ ትራምፕ እንደ ግለሰብ ውርደትን ያከናነበ ነበር፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ለዓለም ያሳየው ዕውነታም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በአፍሪካ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ ተደማጭ አገራት እንኳን ለአሜሪካ አዛዥ-ናዛዥነት አናጎበድድም ማለታቸውን ነው፤ ሲልም ተቋሙ አስነብቧል።

” አሜሪካ ከእንግዲህ የዓለም አለቃ አይደለችም። ይህ ያለፈው ታሪኳ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ በአገራት ላይ ጫና መፍጠርን መርህ ያደረገው አካሄዷ ወደ ፍጻሜው ተቃርቧል፡፡ ይሁንና አሜሪካ ራሷ ይህን ሀቅ ገና አልተገነዘበችውም። ጉልበታቸውን ባለፈውና ባለፈበት መንገድ ለማስቀጠል የመረጡ ነው የሚመስሉት” እንደ UWI እንዳቀመጠው።

“ክስተቱም ግብፅ በአሜሪካ ላይ የጣለችውን ተስፋ ያጨለመ ሆኗል። በቀጣይ ግንኙነታቸው ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችል ነው”::

“መጀመሪያውኑም አሜሪካ እንዲህ ዓይነቱን ውስብስብና በቀላሉ የማይፈታ ዓለም አቀፍ ጉዳይ ወደ ራሷ ወስዳ እንዲያ በአጭር ጊዜ መቋጫ ይበጅለት ማለቷ ነበር ትልቁ ስህተት፡፡

ርምጃው በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ላይ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የሚያሳየውን የጀብደኝነትና የእብሪታዊ አካሄድ ማሳያም ነው። አሜሪካ ራሷን ያገኘችውም ችግር በፍጥነት ለመፍታት እየሞከረች ነው ፡፡ ሆኖም ግን በአዲስ አበባ ላይ ጫና መፍጠሯ ኢትዮጵያውያንን ብቻም ሳይሆን መላ አፍሪካውያንም ከአሜሪካ በተቃራኒ መሰለፋቸው የማይቀር መሆኑን ነው።

ይህ የሚጠቅመው ለአሜሪካም ሆነ ለግብፅ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ነው። ችግሩንም ይበልጥ የሚያወሳስበው ነው የሚሆነው”
“..አሜሪካ ውጤታማ ዲፕሎማሲ አጋር መሆን እንደማትችል በተደጋጋሚ የታየ ሆኗል። “deal of the century” በማለት እስራኤልን ለመርዳት በፍልስጤማውያን ሉዓላዊነት ላይ ጀምራው የነበረውን የተናጠል ጫና መጥቀስ ይቻላሰ። እሱም ቢሆን ውድቅ ሆኗል። እስራኤል የይዞታ ማስፋፋቱን የትራምፕ ዕቅድ በ UAE ስምምነት ለውጣ ሠርዛዋለች። እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብና መሠል አለማቀፍ ችግሮችን ከማደራደር ልትወገድ ነው የሚገባት..”

Click to comment

More in ትንታኔ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top