Connect with us

ቦርዱ በቀጣይ ኮሮና-ተኮር ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

ቦርዱ በቀጣይ ኮሮና-ተኮር ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን አስተላለፈ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ቦርዱ በቀጣይ ኮሮና-ተኮር ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን አስተላለፈ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ፤ የአዋጁ ቀነ-ገደብ ሲጠናቀቅ ሊከሰቱ ይችላሉ ብሎ የሰጋባቸውን እና ትኩረት እንዲሰጥባቸው የለያቸውን ኮሮና-ተኮር ጉዳዮች፣ በ7 የምክረ-ሐሳብ ነጥቦች አስደግፎ ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡

መርማሪ ቦርዱ በቅርቡ በአካሄደው መደበኛ ስብሰባ፤ ከኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ስርጭት አኳያ የአሳሰቡትን ሁኔታዎች በዝርዝር ለይቶ፣ ተገቢ ትኩረት እንዲሁም ጥንቃቄ ሊወሰድባቸው ይገባል የአላቸውን የውሳኔ ሐሳቦች፤ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ እና ለሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ገልጿል፡፡

በዚህም መሠረት ከያዝነው ወር መጨረሻ እስከ መስከረም ወር 2013 ዓ.ም. ማገባደጃ ድረስ፤ በርካታ ሰዎችን ሊያሰባስቡ የሚችሉ ብሔራዊ በዓላት እና ባሕላዊ ክብረ-በዓላት፣ ለኮሮና ቫይረስ መስፋፋት በር ሊከፍቱ ስለሚችሉ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ቦርዱ አሳስቧል፡፡ ሻዴይ፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ)፣ የመስቀል በዓል፣ መውሊድ እና የመሳሰሉት በዓላት በዚህ ጊዜ እንደሚከበሩ የአስታወሰው ቦርዱ፤ ከቫይረሱ ባሕርይ አንጻር ሕብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እንደሚገባውም አስገንዝቧል፡፡

በድጋፍም ይሁን በተቃውሞ፣ ታቅደውም ይሁን በድንገት የሚካሄዱ ሰልፎች እና ስብሰባዎች፤ በግንዛቤ ሥራ እንዲሁም ሕግ በማስከበር ታግዘው መከናወን እንደሚጠበቅባቸው መርማሪ ቦርዱ ጠቁሟል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞም፤ የኀይማኖት ሥነ-ሥርዓትዎች፣ የገበያ፣ የሠርግ፣ የለቅሶ፣ የመዝናኛ እና ሌሎች ሥነ-ሥርዓትዎች ለቫይረሱ መስፋፋት የሚኖራቸው ድርሻ ሰፊ በመሆኑ፤ ይህንኑ ለማስቀረት ከኀይማኖት መሪዎች እና ከኀብረተሰብ አደረጃጀትዎች ጋር ምክክር ማካሄድ እንደሚገባም ቦርዱ ከወዲሁ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም፤ የይቅርታ እና የአመክሮ መስፈርት የሚያሟሉ የሕግ ታራሚዎች ቢለቀቁ በማረሚያ ቤትዎች ከባቢ የሚስተዋለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመቀነስ እንደሚረዳም ቦርዱ በውሳኔ-ሐሳብ ደረጃ አንስቷል፡፡ የሚዲያ ተቋማት ሚናም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ይኼው የቦርዱ ምክረ-ሐሳብ ያስገነዝባል፡፡

በመሆኑም ቦርዱ፤ የአዋጁ ተፈጻሚነት ሲያበቃ አዋጁን ተክተው መንግስት የሚያደርገውን የመከላከል እንቅስቃሴ የሚደግፉ ሕጋዊ አሠራርዎች አስቀድመው ከአልታዩ በቀር፣ ለቫይረሱ የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን በሕግ ለመቆጣጠር ክፍተት ሊፈጠር ስለሚችል፤ አሁን በሥራ ላይ የአሉትን ሕጋዊ አማራጭዎች በግልጽ ማወቅ እና ማሳወቅን አክሎ አዳዲስ እና አጋዥ የሕግ ማዕቀፍዎችም ሊታሰቡ እንደሚገባ በአስተላለፈው ውሳኔ አስረድቷል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ኃላፊነት በያዝነው ወር መጨረሻ ያበቃል፡፡(ፓርላማ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top