Connect with us

ጠ/ሚ ዐብይ እባክዎ የፖል ካጋሜን አገር በድጋሜ ይጎብኟት?!

ጠ/ሚ ዐብይ እባክዎ የፖል ካጋሜን አገር በድጋሜ ይጎብኟት?!
Photo: Social Media

ባህልና ታሪክ

ጠ/ሚ ዐብይ እባክዎ የፖል ካጋሜን አገር በድጋሜ ይጎብኟት?!

ጠ/ሚ ዐብይ እባክዎ የፖል ካጋሜን አገር  ይጎብኟት?! | (ወንድወሰን ውቤ)

“Sometimes in April” በሚል በሩዋንዳው ዘር ጭፍጨፋ ላይ የተሠራ ምርጥ ፊልም አለ። በእኔ እምነት የዘር ጭፍጨፋን አሰቃቂነትና አሳዛኝ ውጤቱን በተገቢው ሁኔታ የሚያሳይ ትምህርት ሰጭ ፊልም ነው። ፊልሙ ላይ በእናታቸው ቱትሲ በአባታቸው ሁቱ የሆኑ ሕፃናት ከሁቱ ገዳዮች ለማምለጥ ኮርኒስ ውስጥ ተደብቀው እያለ አባታቸውን «እኛ ሁቱ ነን ቱትሲ?» በማለት ግራ ያጋባቸውን ግን ወሳኝ ጥያቄ በሹክሹክታ ይጠይቁታል።

የጨነቀው አባት ከዐይኖቹ የሚዘንቡትን የዕንባ ዘለላዎች ለማስቆም እየታገለ «አንድ ቀን ሩዋንዳዊያን ነን እንላለን፤» አላቸው፤ እርሱም በሹክሹክታ። ትንቢታዊ መልስ።

ተማሪዎች በመማሪያ ክፍል ውስጥ ስማቸው አየተጠራ ነገዳቸውን እንዲናገሩ ይገደዱባት በነበረችው ሩዋንዳ ዛሬ ታሪክ ተቀይሯል።

በአሁኗ ሩዋንዳ እንኳን በዘውግ የፖለቲካ ድርጅት መመሥረት ይቅርና «እኔ ሁቱ ነኝ፣ ቱትሲ ነኝ፣ ታዋ ነኝ፤» ብለህ ነገድህን መናገር ወንጀል ነው። ሁሉም ተስማምተውበት «እኛ ሩዋንዳውያን ነን ይላሉ፤» በሹክሹክታ ሳይሆን ጮክ ብለው፣ ከአደጋ ነጻ እንደሆነ በሚያስታውቅ በራስ የመተማመን ስሜት። ሁሉም እምነቶችና ተከታዮቻቸው፣

ሁሉም ቋንቋዎችና ተናጋሪዎቻቸው፣ ሁሉም ባህሎችና የባህሎቹ ባለቤቶች እኩል የሚከበሩባት፣ ማንም ሳይሳቀቅ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚልባት ሀገር ታስፈልገናለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እባክዎ የፖል ካጋሚን ሀገር ይጎብኟት።

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top