Connect with us

ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው

ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው

ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው

~ እጃቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑትም ተደምስሰዋል፣

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ በንጹኃን ዜጎች ላይ ሰሞኑን ጥቃት የፈጸሙ ወንጀለኞችን በሕግ ቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡

በክልሉ በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ጃዲያ ቀበሌ ሐምሌ 20/2012 ዓ.ም በተፈተጸመ ጥቃት የበርካታ ንጹኃን ሕይወት አልፏል፤ የቆሰሉ መኖራቸውን መዘገባችንም ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎም በስጋት ቀጣናዎች ፀረ-ሽምቅና መከላከያ ሠራዊት የሚያደርጉት “ኦፕሬሽን” ተጠናክሮ መቀጠሉንም የክልሉ መንግሥት አስታውቋል፡፡

ችግሩ ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ከፌዴራል እና ከክልል የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ ወንጀሎኞችን ለመያዝ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አብዱላዚም መሀመድ እንዳሉት በወንጀሉ የተሳተፉ ሰዎች በቁጥጥር ሥራ እየዋሉ ነው፡፡ እጃቸውን ለፀጥታ ኃይል ለመስጠት ፈቃደኛ ባልሆኑት ላይ ደግሞ የመደምሰስ ርምጃ መወሰዱንም ምክትል ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ያልተያዙ ወንጀለኞች መኖራቸውን ያመላከቱት ምክትል ቢሮ ኃላፊው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በወንጀሉ የተሳተፉ ወንጀለኞችን በሕግ ቁጥጥር ሥር የማዋል ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡ ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር ሳይውሉ ወደሌላ ሥራ መሠማራት እንደማይቻል የክልሉ መንግሥት አቋም ወስዶ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የወንጀሉ ተሳታፊዎች አሉ በተባለበት ቦታ ስምሪት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በክልሉ አንጻራዊ ሠላም ቢኖርም ማኅበረሰቡ ዘንድ የፀጥታ ስጋት መኖሩን አንስተዋል፡፡ መንግሥት በማኅበረሰቡ ዘንድ ያለውን የፀጥታ ስጋት ለማስወገድ እና ተረጋግተው ሥራቸውን እንዲሠሩ በትኩረት እየሠራ መሆኑንም ነው ያስታወቁት፡፡ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡(አማራ መገናኛ ብዙሃን)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top