Connect with us

አስገድዶ ደፋሪው በ25 ዓመት እሥራት ተቀጣ

አስገድዶ ደፋሪው በ25 ዓመት እሥራት ተቀጣ
Photo: Social Media

ወንጀል ነክ

አስገድዶ ደፋሪው በ25 ዓመት እሥራት ተቀጣ

በአሰገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የ25 አመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት፡፡

ተከሳሽ ደስታ ገበየሁ የተባለ ግለሰብ ቀኑ ነሀሴ ወር 2011 ዓ.ም ዕድሜቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆነ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ክልል ውስጥ በሚገኝው ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመባቸው በመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዐቃቂ ቃሊቲ ምድብ ፅ/ቤት የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627(1) ተላልፎ በመገኘቱ አራት ክሶችን መስርቶበታል፡፡

ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክሱን ክዶ የተከራከረ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ ማስረጃ አቅርቦ በማሰማቱ እንዲሁም ተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ ሊያስተባብል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ ነህ በማለት ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ60 አመት እንዲቀጣ የፈረደበት ቢሆንም የተከሰሰበት ድንጋጌ ጣሪያው 25 ዓመት በመሆኑ በ 25 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሴቶችና ህፃናት ወንጀል ጋር ተያይዞ ከመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ 19 የምርመራ መዝገቦች ቀርበው የተጣሩ ሲሆን በ8 መዝገቦች ላይ ክስ ተመስርቶ ለችሎት መቅረባቸውን የአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ጽፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ሲሳይ ጎኣ የገለጹ ሲሆን ቀሪዎቹ መዝገቦች በምርመራና በመወሰን ሂደት ላይ እንደሆኑ ምክትል ኃላፊ አብራርተዋል፡፡

በመሆኑም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ድርጊቱ ተፈፅሞ ሲያገኝም በተቻለ ፍጥነት ለፓሊስ ማሳወቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡(የፌ/ጠ/ዐ/ሕግ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top