Connect with us

ቅድሚያ ለሀገራዊ አጀንዳ

ቅድሚያ ለሀገራዊ አጀንዳ

ባህልና ታሪክ

ቅድሚያ ለሀገራዊ አጀንዳ

#ቅድሚያ_ለሀገራዊ_አጀንዳ
(ዮሐንስ መኮንን)

ከአምቦ የተገኘችው እና አሁን በሀገረ አሜሪካ የምትኖረው Birhane Beka Geleto አሜሪካዊው አብርሐም ሊንከን እና የኢትዮጵያችን አጼ ምንሊክ እንደሚመሳሰሉባት ጠቅሳ አጼ ምንሊክን አመስግና እንዲህ ስትል ጻፈች፤

• ዘመናዊት ኢትዮጵያን ገንብተዋል፣
• የባርያ ንግድን አስቀርተዋል፤
• የነጭ ተስፋፊዎችን ድል አድርገዋል፤
• የጥቁሮች ነጻነት ምልክት ሆነዋል።

ስለዚህም ለአጼ ምኒሊክ፣ ለጣይቱ፣ ለጎበና ለዲነግዴ፣ ለፊታውራሪ ባልቻ … በርእሰ ከተማችን የመታሰቢያ ሃውልት ሊቆምላቸው ይገባል ስትል በፌስቡክ ገጿ አሳቧን ታካፍላለች።

ለብርሄኔን ጽሑፍ መልስ የሰጡት ከአርሲ የተገኙት በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኤሜሬት አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በፌስቡክ ገጻቸው እንዲህ ብለዋል፤

• ዛሬም ከግብፅና ከሱዳን ጋር የሚያናቁረን የሚንሊክ ጦስ ነው፤
• በአባይ ወንዝ ላይ ከጣና ጀምሮ ምንም ዓይነት ግንባታ ላይገነባ፣ ወይም እንዲገነባ ላይፈቅድ ለእንግሊዞች የፈረመ ምኒልክ ነው፤
• ከሱዳን ጋር መፍታት ያልተቻለው ውስብስቡ የድንበር ችግር የምኒልክ ውርስ ነው፤
• ኢትዮጵያ ዛሬ ወደብ አልባ ሆና የቀረችው ያኔ በተፈፀሙ ታሪካዊ ስሕተቶች ምክንያት ነው፤
• ምኒልክ የዘላለም መከራ አውርሶን የሄደ ጨፍጫፊ ነው፤

(ገጻቸው ላይ ዐይቼ እስካረጋግጥ መጀመሪያ ይህ ጽሑፍ የእርሳቸው መሆኑን አምኜ ለመቀበል ቸቸግሬ ነበር)

#የእኔ_ሃሳብ
_________________

እንደሀገር ባለፍንበት ታሪካችን እና ጀግኖቻችን መስማማት አለመቻላችን አሳዛኙ የትውልዱ ሸክም ይመስለኛል። ወደፊት እንደሀገር ስንሰከን በጥናት እና በምርምር ልብወለዱን ከእውነት ተረቱንም ከታሪክ እንደምንለይ ተሥፋ አደርጋለሁ።

ዛሬ ላይ ግን የአንዱን “ጀግና” አሞግሰን የሌላውን አኮስሰን ለመጨቃጨቅ ጊዜው የሚፈቅድልን አይመስለኝም። ምክንያቱም፤

• ሀገሪቱን ወደተሻለ ዲሞክራሲያዊ የፓለቲካ ኢኮኖሚ ለማሻገር፤
• በሀገር ውስጥ የሚታዩ አለመግባባቶችን በእርቅ እና በውይይት ለመፍታት፤
• የሕዳሴውን ግድብ ለማጠናቀቅ፤
• ኮሮና ቫይረስ ወረረሸኝን ለመከላከል ከፍ ባለ ሀገራዊ ትኩረት ዜጎችን ሁሉ የምናረባርብበት ጊዜ ላይ ነን እና!

ወገናችን እየተሰደደ እና እየተፈናቀለ፣ የገበሬ ጎጆ በጠራራ ፀሐይ በእሳት እየነደደ ይህንን ለማጥፋት እንደመረባረብ፣ ዜጎች በየእለቱ በወረረሽኝ እየረገፉ እና ግብጽ ጦር እየጎሰመች ባለችበት በዚህ አጣብቂኝ ወቅት ሀገራዊ አጀንዳን እንደማስቀደም መቶ ዓመታት ወደኋላ ተመልሶ ባልኖርነበት ዘመን በአጼ ምኒሊክ መነታረክ አእምሮቢስ መሆን ነው።

#ምነው_አምባሳደር ?
______________________

አምባሳደር ሱሌይማንን ከዚህ ቀደም አመስግኜአቸው እንደጻፍኩት ሁሉ በአሁኑ ጽሑፋቸው እንዳዘንኩባቸው ሳልገልጽ አላልፍም። አምባሳደሩን ያዘንኩባቸው ምንሊክን ስለወቀሱ አይደለም። ስንት አንገብጋቢ ሀገራዊ አጀንዳ እያለ 100 ዓመታት ወደኋላ ተመልሰው የንትርክ አጀንዳ በመምዘዛቸው እንጂ!

እንደ ዲፕሎማትነታቸው ማራመድ የሚጠበቅባቸው የሀገሪቱን ኦፊሴላዊ አቋም እንጂ የቡድኖችን ወይንም የግል አመለካከታቸውን መሆን አልነበረበትም። የተረከቡት ኃላፊነት ይህንን በአደባባይ እንዲናገሩት የሚፈቅድላቸው አይመስለኝም።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐብይ ነባር እና አዳዲስ አምባሳደሮችን እና ቆንስላዎችን ሰብስበው የሥራ ስምሪት ሲሰጡ “እናንተ የፓርቲ ተወካዮች አይደላችሁም። የኢትዮጵያ እና የህዝቦቿ ተወካዮች ናችሁ!” ማለታቸውን ሰምተናል። ታዲያ የአንዱን እያሞገሱ የሌላውን እየወቀሱ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በእኩል ተወካይ መሆን ይቻላል?

#ምን_ይደረግ?
______________________

ዲፕሎማቶቻችን ዜጎች ልዩነቶቻችንን በማጥበብ ከላይ የዘረዘርኳቸው አንገብጋቢ ሀገራዊ አጀንዳዎች በድል እንድንሻገር ለሀገራዊ ግዳጅ እንዲያሰልፉን በምንጠብቅበት ወቅት በማያስማሙን አጀንዳዎች እየተጠለፉ እንደ ተራ ዜጋ መጨቃጨቁ ተገቢ አይመስለኝም።


ባለፈው የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሰሃለወርቅ ዘውዴ “የዜጎች በማንነታቸው መታረድ በዘርና በሐይማኖት ተለይቶ መፈናቀል ያሳዝነኛል” ማለታቸው ብጠልጥሎ የጃዋር ግፍ ለምን ተወገዘ ብሎ በአደባባይ ሞገተ። ዛሬ ላይ ደግሞ የዓለማችንን የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ፋና ወጊና አባት በመባል የሚታወቁትን ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክን መርገምና መዝለፍ ጀምረዋል።

Click to comment

More in ባህልና ታሪክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top