Connect with us

“ግብጽ የምታቋርጥ ከሆነ ከዚህ በኀላ ለድርድር አንቀመጥም”- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

"ግብጽ ድርድሩን የምታቋርጥ ከሆነ ከዚህ በኀላ ለድርድር አንቀመጥም"- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
Photo: Facebook

ማህበራዊ

“ግብጽ የምታቋርጥ ከሆነ ከዚህ በኀላ ለድርድር አንቀመጥም”- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ሰሞኑን እየተካሄደ ያለውን የሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር አስመልክተው ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በመግለጫቸው እንዳመላከቱት ግብጽ ከዚህ በፊት በድርድሩ ስታሳየው የነበረውን ሙሉ የዓባይ ውኃ ይገባኛል አካሄድ አሁንም እየተከተለች ነው፡፡

በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመናት የተከተሉት ይህ አካሄድ ለአሁኑ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን በምንም መልኩ የማያስኬድና የማንቀበለው ነው ብለዋል አቶ ገዱ በመግለጫቸው፡፡

ግብጽ አሁንም ፍላጎቷ ድርድሩ እንዲቋረጥ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት በ2015 (እ.አ.አ) ከነበረው የመርህ ስምምነት ውጭ ሌላ መተሳሰሪያ የሌለን በመሆኑ ግብጽ ድርድሩን አቋርጣ የምትወጣ ከሆነ ከዚህ በኋላ ለድርድር የምንቀመጥበት ምንም ዓይነት መንገድ የለም ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡

እየተደራደርን ያለነው ሁሌም እኔ ብቻ ልጠቀም ከምትለው፣ እድሜ ልኳን የኢትዮጵያን ጥቅም ከምትጻረረው፣ ሀገራችን ዘላቂ ጥንካሬ እንዳይኖራት በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከምትሠራው ግብጽ ጋር ነው ሲሉም አቶ ገዱ የግብጽን አቋም አስረድተዋል፡፡
የግብጽ ሕዝብ መንግሥታቸው ምክንያታዊና ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ተመስርቶ እንዲደራደር ጫና እንዲያሳድሩም ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡#አብመድ

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top