Connect with us

በሥርዓተ ቀብሩ ላይ የተገኙ 45 ሰዎች ለይቶ ማቆያ ገቡ

በኮሮናቫይረስ መያዙን ሳያውቁ በሥርዓተ ቀብሩ ላይ የተገኙ 45 ሰዎች ለይቶ ማቆያ ገቡ
Photo: Facebook

ዜና

በሥርዓተ ቀብሩ ላይ የተገኙ 45 ሰዎች ለይቶ ማቆያ ገቡ

በኮሮና ቫይረስ መያዙ ሳይታወቅ ሕይወቱ ያለፈ ሰው የቀብር ሥነ ሥርዓት የፈጸሙና ንክኪ ያላቸው 45 ግሰዎች ወደለይቶ ማቆያ መግባታቸውን የእንሳሮ ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ የሆነ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥሮ ወደ ማቆያ ሳይገባ ናሙና ሰጥቶ ነበር፡፡ ናሙና እንደሰጠ በድንገት ውጤቱ ሳይታወቅ ሕይወቱ አልፏል፡፡ የግለሰቡ ሕይወት እንዳለፈም አስከሬኑ ወደ ትውልድ ቀየዉ ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ተልኳል፡፡

ይህ የሆነው ባለፍነው ቅዳሜ ግንቦት 29/2012 ዓ.ም ነበር፡፡ እስከዚው ቀን ድረስ ውጤቱ ስላልታወቀ ዘመድ አዝማድ ተሰብስቦ አስከሬኑን በመያዝ ወደ እንሳሮ ወረዳ አቅንቶ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ እሑድ ግንቦት 30/2012 ዓ.ም ተከውኗል፡፡ በዚሁ ዕለት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገዉ መረጃ መሠረት ግለሰቡ የኮሮና ቫይረስ እንደነበረበት አረጋግጧል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ መረጃው እንደደረሰዉ ከወረዳው ጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ሰዎች ጋር በመሆን የቀብር ሥርዓቱ በተፈጸመበት እንሳሮ ወረዳ አቅንቶ ከግለሰቡ ጋር ቀጥታ ንክኪ የነበራቸውን ግለሰቦች እየለየ መሆኑን የመምሪያው ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ጸዳሉ ሰሙ ንጉሥ ተናግረዋል፡፡

የእንሳሮ ወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሲስተር በቀለች ሞገስ ደግሞ የቀጥታ ንክኪ ይኖራቸዋል በሚል ጥርጣሬ 45 ሰዎች በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ መደረጉን አስታውቀዋል ሲል አብመድ ዘግቧል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top