Connect with us

ዲና ሙፍቲ በድጋሚ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ

ዲና ሙፍቲ በድጋሚ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ
Photo: Facebook

ዜና

ዲና ሙፍቲ በድጋሚ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሆነው ተሾሙ

 

የኢ.ፌዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበርካታ ዓመታት የዲፕሎማሲ ልምድና ሙያ ያላቸውን አምባሳደር ዲና መፍቲን አዲስ ቃል አቀባይ አድርጎ ሾሟል፡፡

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በካይሮ የኢፌዲሪ ባለ ሙሉስልጣን አምባሳደር በመሆን የነበራቸውን የቆይታ ጊዜ በማጠናቀቅ በቅርቡ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ከዚያ በፊትም መቀመጫቸውን ኬንያ ናይሮቢ በማድረግ በማላዊ፣ በሲሸልስ እና በታንዛንያ የኢፌዲሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። እንዲሁም መቀመጫቸውን በስዊድን ስቶክሆልም በማድረግ በኖርዌ፣ ፊላንድ፣ ዴንማርክ እና አየርላድ የኢፌዲሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። በተመሳሳይ መቀመጫቸውን በዚምባብዌ ሃራሬ በማድረግ በአንጎላ፣ በዛምቢያ፣ በሞዛምቢክ እና በሲሸልስ የኢፌዲሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። ከዚህ በተጨማሪም ዋሽንግተን በሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት እና ካናዳ በሚገኘው የአፌዲሪ ኤምባሲ 3ኛ ጸሀፊ በመሆን በዲፕሎማትነት አገልግለዋል።

በዋናው መ/ቤት ደግሞ የቃል አቀባይ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ የፕሬስና ኢንፎርሜሽን ዳይሬክተር፣ የአፍሪካና የኤዥያ ጉዳዮች 3ኛ ጸሀፊ በመሆን ሰርተዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በከናዳ በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኘነት በማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሰርተዋል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top