Connect with us

በአዲስ አበባ ብሄራዊ አካባቢ በመሳሪያ በታገዘ የዘረፋ ሙከራ ተፈፀመ

በአዲስ አበባ ብሄራዊ አካባቢ በመሳሪያ በታገዘ የዘረፋ ሙከራ ተፈፀመ

ዜና

በአዲስ አበባ ብሄራዊ አካባቢ በመሳሪያ በታገዘ የዘረፋ ሙከራ ተፈፀመ

ዛሬ ረፋድ ላይ በ4፡30 በአዲስ አበባ ብሄራዊ ትያትር ፊትለፊት ወደ ስታዲየም በሚወስደዉ መንገድ ዳር ላይ በሚገኝ አንድ የንግድ ሱቅ ላይ በመሳሪያ ታገዘ የዘረፋ ሙከራ መፈፀሙንና በሁለት ሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን አይን እማኖች ለድሬቲዩብ ገለፁ፡፡

ድርጊቱን ፈጸሙ የተባሉት ሶስት ግለሰቦች ወደ ሱቁ በመግባት በማስፈራራት ዝርፊያ ለመፈፀም እንደሞከሩና በአካባባዉ የነበሩ ሰዎች ሲደርሱባቸዉ የያዙትን ሽጉጥ በመተኮስ በአካባቢዉ ቆሞ ይጠብቃቸዉ በነበረ ተሸከርካሪ ማምለጣቸዉም ታዉቋል፡፡

ዘራፋቹ በተኮሱት ጥይት ሁለት ሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን የገለጹት የአይን እማኖች ዘራፊዎቹ ኮድ 4 ሰሌዳ የተለተፈበት ተሸከርካሪ መጠቀማቸዉንም ገልጸዋል፡፡

የድሬቲዩብ ዘጋቢ ከደቂቃዎች በኋላ በስፍራዉ ሲደርስ ፖሊሶች በአካባዉ እንደደረሱና የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለማፈላለግ መረጃዎችን ሲያሰባስቡ ተመልክቷል፡፡

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top