Connect with us

በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የመኖሩን ሂደት የሚፈትሹ …

በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የመኖሩን ሂደት የሚፈትሹ ከ700 በላይ ቡድኖች በመላው ሀገሪቱ ተሰማሩ
Photo: Facebook

ዜና

በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የመኖሩን ሂደት የሚፈትሹ …

ኮቪድ19 ሥርጭትን ለመከላከል የተቋቋመውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰብሳቢነት ሥራውን የሚከውነው የሚኒስትሮች ኮሚቴ ትናንት ጠዋት ስብሰባ አካሂዷል፡፡

እስካሁን በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ የክንውን ሂደቱም ተገምግሟል፡፡ በስብሰባው ወቅት የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል፡።

67 በመቶ የሚሆኑት አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በአዲስ አበባ የሚገኙ መሆኑ፣ ቫይረሱ በማኅበረሰቡ መካከል መዛመቱን እንደሚያሳይም ተመላክቷል፡፡

ቤት ለቤት የሚካሄደው የሙቀት ልኬት እና የቫይረሱን ምልክቶች የመለየት ሥራ እንዳለ ሆኖ፣ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የመኖሩን ሂደት የሚፈትሹ ከ700 የሚበልጡ ቡድኖች በመላው ሀገሪቱ ተሠማርተዋል ነው የተባለው፡፡

የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ንዑስ ኮሚቴ እንዳስታወቀው፣ የመንግሥት ተቋማት በአካል ተገናኝተው በሚያካሂዷቸው ስብሰባዎች ምትክ የሚከናወኑ በቴክኖሎጂ የታገዙ ስብሰባዎች በጥሩ ሁኔታ እየተካሄዱ ነው፡፡

በ11 ተቋማት ውስጥ ለወትሮው ገጽ ለገጽ የሚሰጡ 75 መንግሥታዊ የሆኑ አገልግሎቶችም፣ አሁን በኢንተርኔት በመታገዝ እየተካሄዱ ነው ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ፣ ሌሎቹም ንዑሳን ኮሚቴዎች ዋና ዋና ክንውኖችን እንዲሁም ተግዳሮቶችን የገለጹ ሲሆን፣ በተለይም በማኅበረሰቡ ዘንድ የሚታየው ቸልተኝነት ትኩረት ተደርጎበታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመላው ሀገሪቱ የምርመራ ዐቅም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰባቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም፣ ወረርሽኙን ከመመከት ጎን ለጎን፣ በዐበይት ዘርፎች ምርታማነትን ማስቀጠል እጅግ አስፈላጊ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡(አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top