Connect with us

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 8 የተሰረቁ ተሽከርካሪዎችን ከነተጠርጣሪዎቹ መያዙን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 8 የተሰረቁ ተሽከርካሪዎችን ከነተጠርጣሪዎቹ መያዙን አስታወቀ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 8 የተሰረቁ ተሽከርካሪዎችን ከነተጠርጣሪዎቹ መያዙን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 8 ተሽከርካሪዎችን ከ16 የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች ጋር ይዞ ምርመራውን እያጣራ መሆኑን አስታወቀ።

በኮሚሽኑ የልዩ ልዩ እና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ እንደገለጹት በከተማዋ የሚከናወነውን የመኪና ስርቆት ለመቆጣጠር የተለያዩ የቅንጅት ስራዎች ተከናውነዋል።

ይህም የተጠናከረ ስራ ቀጥሎ በተለያዩ ጊዜያት የተሰረቁ 8 ተሽከርካሪዎች ከ16 የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው በመጣራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

የክትትልና የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ በመቀጠሉ በመዲናዋ በተለይ የመኪና ስርቆት ወንጀል እየቀነሰ መምጣቱንም ተናግረዋል።

በተለይ የኮድ 2 ሰሌዳ ያላቸው አንዳንድ ግለሰቦች በድብቅ እያከራዩ የሆነ አጋጣሚ ሲፈጠር ተሰረቀብን በማለት ማመልከታቸውንም ደርሰንበታል ብልዋል።

የእነዚህ ግለሰቦች ጉዳይ ሲጣራ ግን ስርቆት ሳይሆን የማታለል አለበለዚያም እምነት ማጉደል ሆኖ መገኘቱንም አስረድተዋል።

አንዳንዶችም መኪናቸውን በሚያቆሙበት ወቅት ቸልተኝነትና ጥንቃቄ የጎደለው መሆኑ ለስርቆት የሚዳርግ መሆኑን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

ሆኖም በአዲስ አበባ የመኪና እና መሰል የስርቆት ወንጀሎችን ለመከላከል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

በፖሊስ ብርቱ ጥረት የተሰረቁት ተሽከርካሪያቸው የተመለሱላቸው ግለሰቦችም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ:- ኢዜአ

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top