Connect with us

“ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እየሰራሁ ነው”  ፖሊስ

"ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እየሰራሁ ነው" ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

ዜና

“ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እየሰራሁ ነው”  ፖሊስ

“ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እየሰራሁ ነው”  ፖሊስ

በወጣት ቴዎድሮስ አበባው ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎችን ለማወቅና ለመያዝ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በአጭር ቀናት ውጤቱን ለህዝብ እንደሚያሳውቅም ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡     

ወጣት ቴዎድሮስ አበባው መጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ/ም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ቤተል አዲስ ተስፋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግምት ከምሽቱ 5 ሰዓት ገደማ ባልታወቁ ሰዎች በተፈፀመበት ወንጀል ህይወቱ አልፎ በመገኘቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

 በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ግለሰቦች ላይ ተመሳሳይ ወንጀሎች ተፈፅመው ፖሊስ ባደረገው ክትትል ፈፃሚዎቹን በአጭር ቀናት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሎ ለህዝብ ይፋ ማድረጉን ያስታወሰው ኮሚሽኑ በተለይም የግል ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡ አሽከርካሪዎች እና ተሽከርካሪዎች ላይ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 8 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ መጋቢት 07 ቀን 2013 ዓ/ም በኮሚሽኑ የፌስቡክ ገፅ መረጃ ማሰራጨቱን ጠቅሷል፡፡ 

የግል ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ስራ ላይ የተሰማራው የወጣት ቴዎድሮስ አበባውን ህይወት ያጠፉ ተጠርጣሪዎችን ለማወቅና ለመያዝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቀን ከሌሊት ክትትል እያደረገ ሲሆን በአጭር ቀናት ውስጥ የደረሰበትን ውጤት ለህዝቡ እንደሚያሳውቅ  ገልጿል ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ለሚያስፈልጉ መረጃ እና ማስረጃዎች  ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ኮሚሽኑ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top