Connect with us

“ሥልጣኔን አልለቅም… “ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም

"ሥልጣኔን አልለቅም... "ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም
Photo: Social media

ማህበራዊ

“ሥልጣኔን አልለቅም… “ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም

“ሥልጣኔን አልለቅም… “ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም

(ታምሩ ገዳ)

የአለም ጤና ድርጅት፣ (WHO ) ዋና ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ከድርጅታቸው ጋር ሰሞኑን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አስጣ አገባ ውስጥ የገባው እና ለተቋሙ የሚያደርገውን የገንዘብ እገዛ እንደሚያቋርጥ የገለጸው የአሜሪካ አስተዳደር ሀሳቡን እንደሚቀይር ፣ እርዳታውም የሚጠቅመው ሌሎች አገራትን ብቻ ሳይሆን አሜሪካንንም ጭምር ለመታደግ እንደሚውል ተስፋቸውን ገለጹ፣ከስልጣን ይለቁም እንደሆን ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ።

መቀመጫውን በጀኔቭ፣ ስዊዘርላንድ ያደረገው የአለማቀፉ የጤና ተቋም ኃላፊው ዶ/ር ቴዎድሮስ በወቅታዊው የኮሮና ፣ሳንባ ቆልፍ ወረርሽኝ ዙሪያ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ድርጅታቸው ወረርሽኙን በተመለከተ ደባብቋል፣ አፍቃሪ ቻይና የሆነ የተሳሳታ መረጃን አናፍሷል የሚለው ውንጀላን ተከትሎ አንዳንድ የአሜሪካ የሪፐብሊካን ፓርቲ የህዝብ እንደራሴዋች ባለፈው ሳምንት ” ፕ/ት ትራምፕ ለጤና ተቋሙ በዚህ አመት የገንዘብ ፈሰስ እንዲያደርጉ ከተፈለገ ዶ/ር ቴዎድሮስ በቅድሚያ ከሀላፊነት በፍቃደኝነት መውረድ አለባቸው”የሚለውን ጥሪን ከግንዛቤ ውስጥ በመክተት ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

ዶ/ር ቴዎድሮስ ሲመልሱ ” የተያያዝኩትን ስራ ቀንም፣ ማታም መስራቱን እገፋበታለሁ ። ምክንያቱም የተቀበልኩት ኃላፉነት የሰዎችን ህይወትን ማትረፍ እና በረከትነትም ስለ አለው ነው፣ትኩረቴም እዚያ ላይ ይሆናል”ብለዋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ የሚመሩት ተቋም በወረርሽኙ ሳቢያ በተከተላቸው የተለያዩ ፖሊሲዎች የተነሳ “ዶ/ር ቴዎድሮስ ብቁ ባለመሆናቸው ስልጣን ባስቸኳይ ይልቀቁ የሚሉ እና ይህንን አቋም የሚቃወሙ” ሁለት ጎራዎች ሰሞኑን ተስተውለዋል ።

ይህ በዚህ እንዳለ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ማይክል ፖምፔዬ ባለፈው ሚያዚያ 22/2020 እኤአ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አገራቸው ለተለያዩ አገራት ለጸረ ኮሮና ዘመቻ የሚውል ወደ ሰባት ሚሊዮን ዶላር እንደምትስጥ የጠቆሙ ሲሆን አንዳንድ የህዝብ እንደራሴዎችም አሜሪካ ለአለም ጤና ተቋም የምትለግሰው ገንዘብ ለአገራቱ በተናጠል እንዲስጥ ሲሉ ጠይቀዋል።

በተያያዘ ዜና የኮሮና ወረርሺኝ መነሻ አገር የሆነችው እና በወረርሽኙ ሳቢይ ከፕ/ት ትራምፕ አስተዳደር ጋር በቅርቡ አተካሮ ውስጥ የገባችው ቻይና የአለማቀፉ የጤና ተቋም ወረርሽኙን ለመዋጋት በሚያደርገው ዘመቻ ይረዳ ዘንድ በትላንትው ዕለት የሰላሳ ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ እገዛ ማድረጓን በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃለች። ቻይና ባለፈው መጋቢት ወር ሀያ ሚሊዮን ዶላር መለገሷን የሮይተርስ ዜና አገልግሎት አውስቷል።

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top