Connect with us

የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ደረሰ

የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ደረሰ

ጤና

የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 105 ደረሰ

105 ደርሰናል!!

ባለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ ከተደረገላቸው 659 ሰዎች መካከል 9 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። በዚህም መሠረት በበሽታው የተያዙ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 105 ደርሷል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው መካከል 8 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የኢኳቶሪያል ጊኒ ዜግነት ያለው ነው።

በጠቅላላው ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 105 መድረሱን ገልጸዋል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ ስድስቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ ሶስቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ የነበራቸው ናቸው።

አራቱ ከአዲስ አበባ ሲሆኑ ሶስቱ ከጅቡቲ መጥተው በድሬዳዋ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆን አንድ የጅማ ከተማ ነዋሪ ነው።

አንድ ታማሚ ያገገመ ሲሆን አንድ ደግሞ በጽኑ ህሙማን ውስጥ ይገኛል።

እንደ አገር 84 በኮሮናቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሆነ ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።
#ኢዜአ

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top