Connect with us

ከውጭ የሚገቡ እንግዶች ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት ይገለላሉ

ከውጭ የሚገቡ እንግዶች ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት ይገለላሉ
Photo: Facebook

ዜና

ከውጭ የሚገቡ እንግዶች ከዛሬ ጀምሮ ለ14 ቀናት ይገለላሉ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ከዛሬ ጀምሮ ከውጭ አገር የሚገቡ እንግዶች ለ14 ቀናት በራሳቸው ወጪ በሆቴል ቆይታ በማድረግ ጤንነታቸውን የማረጋገጥ ሥራ እንደሚከናወን ተጠቆመ።

ከዛሬ መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በተወሰነው መሰረት በተለያየ መንገድ፣ ለተለያየ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ውጭ የነበሩ ወገኖች (የውጭ አገር እንግዶችን እንደሚጨምር ታውቋል) ወደ ኅብረተሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት ሁለት ሳምንታት ለየት ብለው የሚቆዩባቸውን ስፍራዎች መሰናዳታቸውን የአዲስአበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በማህበራዊ ድረገፃቸው ይፋ አድርገዋል።

ከመንግሥት በተገለጸው መሠረት ለማረፊያ እንዲሆኑ የአየር መንገዱ ስካይላይት ሆቴል እና ግዮን ሆቴል መዘጋጀታቸውን መነገሩን ተከትሎ “ገንዘብ የሌላቸው እንግዶች ምን ሊሆኑ ነው” የሚል ጥያቄን አስነስቷል።

ሆኖም ም/ከንቲባ ታከለ በቆይታ ጊዜው ወጪያቸውን ለመሸፈን ለማይችሉ ዜጎች ሙሉ ወጪያቸውን መንግሥት እንደሚሸፍን አረጋግጠዋል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top