Connect with us

ትግራይ ለሥርዓት የሚገዛ ሕዝብ መኖሪያ፤ የኢትዮጵያዋ ቻይና-አስደናቂ የተሞክሮ ማዕከል

ትግራይ ለሥርዓት የሚገዛ ሕዝብ መኖሪያ፤ የኢትዮጵያዋ ቻይና-አስደናቂ የተሞክሮ ማዕከል
Photo: Facebook

ጤና

ትግራይ ለሥርዓት የሚገዛ ሕዝብ መኖሪያ፤ የኢትዮጵያዋ ቻይና-አስደናቂ የተሞክሮ ማዕከል

ትግራይ ለሥርዓት የሚገዛ ሕዝብ መኖሪያ፤ የኢትዮጵያዋ ቻይና-አስደናቂ የተሞክሮ ማዕከል
(ከሰለሞን ሃይሉ)

ትግራይ ሥርዓት ማስከበር ቀላል ነው፡፡ የጥይት ድምጽ አይሰማም፤ የህግ የበላይነት አለ፡፡ ህዝቡ በቀላሉ የሚነገረውን ይቀበላል፡፡ በትግራይ ተፈጥሮን ለመጠበቅ የሚሰሩ ስራዎች ያገጠጡ ተራሮችን አረንጓዴ እንዲለብሱ ማድረግ የቻለው የእውነት ለለውጥ እሺ የሚል ህዝብ መኖሪያ በመሆኑ ነው፡፡

የትግራይ ክልል ኮሮናን ለመከላከል በርካታ ስራዎችን እየሰራ ነው፡፡ እንደሌሎች አካባቢዎች ህወሃት በዚህ ሰዓት ስብሰባ ብላ ማንንም አትጠራም፡፡ ህዝብ በጋራ የሚሆንባቸው መንገዶች ቀንሰዋል፡፡ ጥንቃቄው አይሏል፡፡ የእኩለ ጾም ሰንበት የቅዳሴ ሥርዓት የዚህ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡

ቅዱስ ሲኖዲዮስ በተቻለ መጠን ምዕመናን በተራራቀ አግባብ ቆመው ቅዳሴ እንዲያስቀድሱና መጨናነቅ እንዲቀንስ የሚል መመሪያ አስተላልፎ ነበር፤ እውነት ለመናገር የዋና ከተማዋን ቤተ ክርስቲያናት የትናንትና ውሎ ለተመለከተ መልዕክቱ ከዚህ በተቃራኒው ይመስል ነበር፡፡ ትግራይ ግን አስገራሚ ነገር ታየ፤ ብዙ ቤተ ክርስቲያናት የቅዱስ ሲኖዲዮሱን ትዕዛዝ አከበሩ፤ የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ እያንዳንዱ ሰው ባለቤት ሆነ፤ ድንቅና በቻይና ብቻ ባየነው ትዕዛዝን የማክበር ባህል ቅዳሴ ያስቀደሱት ምዕመናን አቋቋማቸው የሚደንቅና ርቀትን የጠበቀ ነበር፡፡

ትግራይ የኢትዮጵያ ቻይና ሆናለች፡፡ የምርጥ ተሞክሮ ቀጠና መሆኗን ለመቀበል የሚቸገሩ ብዙ ቢሆኑም እውነታው ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው፤ ስርዓት ወዳድ የሆነው ህዝብ በቀላሉ የሚባለውን ተቀብሎ ለመተግበር አያንገራግርም፤ ይሄ ደግሞ ፍትሕ እንዲኖር፣ ጤና ትምህርትና ግብርናን የመሳሰሉ ልማቶች ስኬታማ እንዲሆኑ እያገዘ ነው፡፡

የተንታኝ ግሽበት የተግባሪ እጥረት ያየንበት ኮሮና

የለውጥ ሃይሎች አንገሸገሸን ያሉትን ስርዓት ጣልነው ቢሉም ካንገሸገሻቸው ተግባር አላረፉም፡፡ ህወሃት ተባራበታለች የተባሉ አካባቢዎች ዛሬ ተኩስ የማይለያቸው፣ ወጥቶ መግባት ብርቅ የሆነበት ሹመኛ በጠራራ ጸሐይ የሚገደልበት ንግድና ትምህርት የቆመባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ሰላሳ ጊዜ ተከፍተው ሰላሳ ጊዜ የተዘጉባቸው ናቸው፡፡

ጭቆናን ገረሰስን የሚሉ አካባቢዎች እረኛ ጭምር የሚታገትባቸው፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታፍነው የገቡበት የማይታወቁበት ሆነዋል፡፡ አሁንም ፖለቲካ መጥፎውን እንዳንቀርፍ ጥሩውን ልምድ እንዳንለዋወጥ አድርጎን እንጂ ከትግራይ ህዝብ እሴቶች ልንማር የሚገባቸው በርካታ መልካም ልምዶች አሉ፡፡ ምስጋና ለዚህ ትሁትና ታዛዥ ህዝብ ይሁን!!

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top