Connect with us

“ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኮሮናን በመዋጋት ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ያሉ መሪ” ሲል ቢቢሲ አደነቀ

“ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኮሮናን በመዋጋት ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ያሉ መሪ” ሲል ቢቢሲ አደነቀ
Photo: BBC

ጤና

“ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ኮሮናን በመዋጋት ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ያሉ መሪ” ሲል ቢቢሲ አደነቀ

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር በመሆንእያገለገሉ ያሉትን ኢትዮጵያዊ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በዚህ ከባድ ወቅት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ያሉ ታላቅ ሰው በማለት ጠቅሷቸዋል።

ዶክተር ቴዎድሮስ የስርጭት አድማሱን እያሰፋና በተለያዩ የዓለም ሀገራት እየተስፋፋ ያለውን ኮሮና ቫይረስ አስጊ በሆነበት በዚህ ጊዜ ሃላፊ መሆን ፈታኝ ቢሆንም በትኩረት እየሠሩ ነው ብሏል ዘገባው፡፡

የዶ / ር ቴድሮስ የሥልጣን ዘመን በመጀመሪያ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በተከሰተው ኢቦላ አሁን ደግሞ በኮሮና የተፈተነ ቢሆንም ዶክተር ቴዎድሮስ ግን ጠንክረው በመስራት ላይ መሆናቸው ሚያስመሰግናቸው ነው ሲል ገልጿል፡፡

ሁለቱም በሽታዎች ለአለም የጤና ድርጅትም ሆነ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ድንገተኛ አደጋዎች እንደሆኑም አስነብቧል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ ከሁለት አመት በፊት ወደ ሃለፊነት የመጡ ሲሆን በየአመቱ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆኑትን ወባ፣ ኩፍኝ፣ የሳንባ ምች እና ኤችአይቪ ለመቀነስ እየሠሩ እንደሚገኙ ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top