Connect with us

እናቶች ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ህፃናትን አስጠግተው ማቀፋቸው የህፃናቱን በህይወት የመቆየት እድል ይጨምራል-ጥናት

እናቶች ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ህፃናትን አስጠግተው ማቀፋቸው የህፃናቱን በህይወት የመቆየት እድል ይጨምራል-ጥናት
Photo: Facebook

ጤና

እናቶች ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ህፃናትን አስጠግተው ማቀፋቸው የህፃናቱን በህይወት የመቆየት እድል ይጨምራል-ጥናት

ዝቅተኛ ክብደት ይዘው የሚወለዱ አዲስ ሕፃናትን ቀኑን ሙሉ ማቀፍ የህፃናቱን በህይወት የመቆየት እድል እንደሚጨምር ጥናት አመለከተ፡፡

ካንጋሮ ልጇን በሆዷ ስር ከምታቅፍበት ስርዓት ጋር በመያያዝ አስተቃቀፉን ወይም ዘዴውን ካንጋሮ የሚል ስያሜን አግኝቷል፡፡

እናቶች ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ህፃናትን በጨርቅ ወይም የህፃናት ማዘያን በመጠቀም ወደ ሰውነታቸው በማስጠጋት ማቀፋቸው በመጀመሪያው ወር በህይወት የመቆየት እድላቸውን በ30 በመቶ እንዲሁም በስድስት ወራት ውስጥ 25 በመቶ መጨመሩን ጥናቱ ማመላከቱን በኖርዌይ ቤርጋን ዩኒቨርሲቲ የእናቶችና የህፃናት ጤና ማእከል ውስጥ የሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፌሰር ሀልፎር ሶመርፌልት ገልጸዋል፡፡

ይህ የጥናት ቡድን በዓለም ላይ ከፍተኛው ቁጥር ያለው ዝቅተኛ ክብድት ያላቸው ህፃናት በምታስመዘግበው ህንድ ውስጥ ከፈረንጆቹ 2015 እስከ 2018 ድረስ 8 ሺህ 400 በሚሆኑ ዝቅተኛ የወሊድ ክብደት ባላቸው ሕፃናት ላይ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ሕፃናት ከሌሎች ሕፃናት በበለጠ ለበሽታ እና ለሞት የተጋለጡ መሆናቸውን ያመለከተው የጥናት ቡድኑ ካንጋሮ እንክብካቤን መተግባር የህፃናቱን በህይወት የመቆየት እድል ይጨምራል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-www.upi.com

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top