Connect with us
አ/አ ፖሊስ ኮምሽን

ወንጀል ነክ

የፖሊስ ማሳሰቢያ ~ ለሆቴሎች፣ ፔንሲዮኖች…

ወንጀልና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሌሎች የፀጥታ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል መኖሪያ ቤት እና የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ልዩ ልዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነት እንዲያረጋግጡ የአ/አበባ ፖሊስ አሳሰበ፡፡

በከተማችን አ/አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ማንነታቸውን ሰውረው መኖሪያ ቤቶችንና መኝታ ቤቶችን በመከራየት ወንጀል ለመፈፀም አቅደው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ስለመኖራቸው የፖሊስ የምርመራ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡
የከተማችንን ሠላም በዘላቂነት ማስቀጠል የተቻለው በፀጥታ አካላት ቁርጠኝነት እና በህብረተሰቡ የነቃ ወተሳትፎ መሆኑን የገለፀው የአ/አበባ ፖሊሰ አሁንም ይህንን ሰላም አሰተማማኝ አድርጎ ማቆየት እንዲቻል ከመቼውም ጊዜ በላይ ለፀጥታ ስራ ልዩ ትኩረት መስጠት የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብሏል፡፡

የአ/አበባ ፖሊስ ከህብረተሰቡና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገልፆ ወንጀል ፈፃሚዎችና ሌሎች የፀጥታ ችግሮችን ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ምቹ ሁኔታ እንዳይኖራቸው ማድረግ ተገቢ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡
ይህንን ለማሳካት በዋናነት የመኖሪያ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች ፤የመኝታአገልግሎት በሚሰጡ፡ ሆቴሎች፡ ፔንሰሊዮኖችና ተመሣሣይ አገልግሎት የሚሰጡ የንግድ ቤቶች ማንነታቸው በግልፅ ላልታወቁ ሰዎች ቤት እንዳያከራዩ እንዲሁም በሚያከራዩበት ወቅት የተከራዩን ማንነት የሚገልፁ የነዋሪነት መታወቂያና ሌሎች ሰነዶችን በሚገባ አረጋግጠው በመመዝገብ ይህንንም በየአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው የአ/አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

የጥፋት ተልኮ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱና ለአካባቢያቸው እንግዳ የሆኑ ፀጉረ ለውጦች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያቸው ለሚገኙ የፀጥታ አካለት ጥቆማና መረጃ እንዲሰጡ ፖሊስ ጠይቋል፡፡ ለከተማችን ሠላምና ፀጥታ መረጋገጥ ህብረተሰቡ የበኩሉን ሚና በመወጣት አጋርነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በስልክ ቁጥሮች
• የፌ/ፖሊስ 011-512-63-03፣011-552-6306፣ነፃ ጥሪ 987
• አ/አበባ ፖሊስ 011-111-01-11 ነፃ ጥሪ 991
• ቦሉ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-66-74-618
• አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-273-3743
• ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-371-7753
• ን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 011-443-15-29
• አራዳ ፖሊስ መምሪያ 011-573-426
• ልደታ ፖሊስ መምሪያ 011-5153760
• ጉለሌ ፖሊስ መምሪያ 011-1575059
• የካ ፖሊስ መምሪያ 011-618-33-39
• ቂርቆስ ፖሊስ መምሪያ 011-552-8044
• አቃቂ ፖሊስ መምሪያ 011-439-14-37
• የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ 011-66-28-086 እና በነፃ መስመር 6727
• በተጨማሪም ከየካ ክ/ከተማ የተካለሉ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ነዋሪዎች በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና ከቦሌ ክ/ከተማ የተካለሉ የለሚኩራ ክ/ከተማ ነዋሪዎች .በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመረጃ መቀበያ ስልኮች ደውሎ በማሳወቅ እንዲተባበሩ የአ/አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top