Connect with us

በክላሽ ጓደኛዉንና የቀድሞ ፍቅረኛዉን ተኩሶ የገደለዉ ፖሊስ ተቀጣ

ፍርድ ቤት የምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባርን ከፓርቲነት መሰረዙ አግባብ ነው አለ
ፌ/ጠ/አ/ህግ

ወንጀል ነክ

በክላሽ ጓደኛዉንና የቀድሞ ፍቅረኛዉን ተኩሶ የገደለዉ ፖሊስ ተቀጣ

በክላሽ ጓደኛዉንና የቀድሞ ፍቅረኛዉን ተኩሶ የገደለዉ ፖሊስ ተቀጣ

ጉዳዩ የተፈፀመዉ እዚሁ አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዬ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ክልል ልዩ ቦታዉ ኮልፌ ፖሊሰ ካምፕ ዉስጥ ነዉ፡፡ ተከሳሽ ኮንስታብል እንዳልኬ አስረዳ ይባላል የ23 አመት ወጣት ነዉ ይህዉ ወጣት ህግ አስከባሪ የስራ ባልደረባዉን የቀድሞ ፍቅረኛዬን ሌላ ሚስት አለዉ በማለት የሀሰት ወሬ በማዉራት ከእኔ ጋር አለያይቶ የራሱ አድርጓታል በዚህም ምክንያት ተጣልተን ጥርሴን አዉልቆ የታረቅን ቢሆንም በዚሁ ምክንያት ሟችና የድሮ ፍቅረኛዬ ሁሌ ይስቁብኛል ሲል ቂም ይዞ ቆይቷል፡፡ 

ቂም ቋጥሮ የነበረዉ ኮንስታብል ግን ነገሩን በቀላሉ ሊቋጨዉ አልፈለገም ቀድሞ ይዘጋጅና ለስራ በተሰጠዉ ታጣፊ ክላሽ ፍቅረኛዬን ቀምቶኛል ያለዉን ሟች ም/ሳጅን ሃብቴ ልንገረዉን ሁለቴ በመተኮስ ልቡና ሳምባዉ ላይ በመምታት ህይዎቱ እንዲያልፍ ያደርገዋል፡፡ ተከሳሹ በዚሁ ሳያበቃ የድሮ ፍቅረኛዉን ኮንስታብል ትእግስት አማረንም አንገቷ ስርና እግሯ ላይ በመምታት ብዙ ደም ፈሷት የልብና የትንፋሽ ስርአቷ በማቆሙ ምክንያት ህይዎቷ እንዲያልፍ አድርጓል፡፡ 

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግም የወንጀል ህግ አንቀፅ 539/1/ሀ/ ላይ የተመለከተዉን በመተላለፍ በፈፀመዉ ከባድ ሰዉ የመግደል ወንጀል ሁለት ክሶችን መስርቶበት የክርክር ሂደቱ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ ተከሳሽ ድርጊቱን ፖሊስ ሆኖ ሳለ የተሰጠዉን እምነት በማጉደል የፈፀመ መሆኑ በአንድ የቅጣት ማክበጃነት በመያዝና ከዚህ በፊት ሪከርድ የሌለዉ መሆኑ፣ ተከሳሽ ድርጊቱን መፈፀሙን ማመኑ ፣በህመም እየታከመ የሚገኝ መሆኑ፣ድርጊቱን የፈፀመዉ የተከሳሹ ስሜት የሚነካ ተግባር ተፈፅሞበት መሆኑና በጥቅሉ ሰባት የቅጣት ማቅለያዎች ተይዘዉለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በቀን 22/06/2013 ዓ.ም ባስቻለዉ ችሎት ወንጀለኛዉ በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡(ፌ/ጠ/አ/ህግ)

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top