Connect with us

በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ አካባቢ የተከሰተው የጸጥታ ችግር አሁንም አልተሻሻለም

አጣዬ-ችግር የማያጣው ቀጠና!
አብመድ

ዜና

በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ አካባቢ የተከሰተው የጸጥታ ችግር አሁንም አልተሻሻለም

በሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ አካባቢ የተከሰተው የጸጥታ ችግር አሁንም አልተሻሻለም

የአማራ መገናኛ ብዙሀን በስልክ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተናገሩት መጋቢት 11/2013 ዓ.ም በአጣዬ ከተማ ምሽቱ ጸጥ ብሎ ነው ያደረው፤ መጋቢት12/2013 ዓ.ም ከንጋት 11፡00 ገደማ ጀምሮ ግን ጠንከር ያለ ተኩስ እየተካሄደ ነው፡፡ 

በግለሰቦች እጅ ሊያዙ የማይችሉ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ጭምር ወደ ነዋሪው እየተተኮሱ መሆኑን ነው የዓይን እማኞች የነገሩን፡፡ ንብረት መዘረፉን፣ ቤት መቃጠሉን፣ የሰው ሕይወት መጥፋቱን ገልጸዋል፡፡ የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎችም በአቅራቢያ ወደሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች እየሸሹ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ትናንት መጋቢት 11/2013 ዓ.ም ወደ ስፍራው የገባው የመንግሥት የጸጥታ ኀይል ውጥረቱን ለማርገብ ጥረት እያደረገ ቢሆንም ችግሩ ግን እንደቀጠለ ነው ብለዋል፡፡ አሁንም በካራ ቆሬ፣ በማጀቴ፣ በሰንበቴና በጀዋሀ የጸጥታ ስጋት እንዳለባቸው ነው አስተያዬት ሰጪዎቹ የተናገሩት፡፡

ዛሬ ማለዳ ሽብር ፈጣሪው የተደራጀ ኀይል ማጄቴ ከተማን እንደከበባት አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል፡፡ የከተማው ነዋሪም በሥጋቱ ምክንያት ከከተመዋ እየወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ እንዳሉት የአካባቢው የጸጥታ ኃይል ሽብር ፈጣሪውን የተደራጀ ኀይል  ለመመከት ጥረት እያደረገ ነው፡፡

በማጀቴ ባለፈው ረቡዕ ነበር የተኩስ ልውውጡ የተጀመረው፡፡ በማግስቱ የፌዴራል ፖሊስ ወደ ቦታው ከገባ በኋላ መረጋጋት ቢኖርም ትናንት መጋቢት11/2013 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ሽብር ፈጣሪዎቹ ወደ ማጀቴ ተጠግተው ውጊያ መክፈታቸውን የከተማው ነዋሪዎች በስልክ ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው የጸጥታ ኃይል ትናንት መጋቢት 11/2013 ዓ.ም ቢመክታቸውም በድጋሜ ኀይላቸውን አጠናክረው መጠጋታቸውን አንስዋል፡፡ ሽብር ፈጣሪዎቹ የተደራጁና ከባድ መሳሪያ የታጠቁ በመሆኑ የኀይል አለመመጣጠን መኖሩን ተናግረዋል፡፡

በስፍራው በቂ ኃይል ሊመደብ እና ተገቢው ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ነዋሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡ አብመድ ነዋሪዎቹን በስልክ በሚያነጋግረበት ወቅትም የተኩስ ድምጽ ይሰማ ነበር፡፡

የክልሉ መንግሥት በሰጠው መግለጫ ግጭቱ ሐሙስ መጋቢት 09/2013 ዓ.ም ምሽት ጅሌ ጥሙጋ ላይ በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ጠብ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት ህልፈትን ምክንያት በማድረግ የተቀሰቀሰ ነው ብሏል፡፡ በግለሰቦች መካከል የነበረውን ግጭትና የደረሰውን ሞት ምክንያት በማድረግም በሀገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች እርቅ ተፈጽሞ እንደነበር ጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ ከዓርብ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ጀምሮ በከባድና የቡድን መሣሪያ ጭምር በመታገዝ የተደራጀና ብዛት ያለው የታጠቀ ኃይል በአጎራባቹ የሰሜን ሸዋ ዞን አጣየ ከተማና አካባቢው ሠላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል፡፡ ችግሩን ለመቆጣጠርም ከፌደራል መንግሥት ጋር በመሆን ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡

በአጣየና በአካባቢው የተፈጸመውን ዝርዝር ጥቃት፣ የደረሰውን ሰብዓዊና የንብረት ጉዳት መንግሥት በፍጥነት መረጃውን አጣርቶ ለሕዝቡ ይፋ እንደሚያደርግም የክልሉ መንግሥት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ (አብመድ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top