Connect with us

“ሕዝቡ… ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ አለበት”

"ሕዝቡ... ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ አለበት"
አብመድ

ነፃ ሃሳብ

“ሕዝቡ… ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ አለበት”

“ሕዝቡ… ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ አለበት”

የአማራ ክልል ሠላምና ደኅንነት ቢሮ

የአማራ ክልል ሠላምና ደኅንነት ቢሮ ኀላፊ ሲሳይ ዳምጤ በሰሜን ሸዋ ዞን የተከሰተውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አጣዬ፣ ሸዋሮቢትና ሰንበቴ አካባቢዎች ተደጋጋሚ የጸጥታ ችግር ይከሰት እንደነበር በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡ ቀደም ብሎ በጸጥታ ችግሩ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል፡፡ በቅርቡም ከሕዝቡ ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ምሽት አንድ ግለሰብ በጥይት መገደሉን ተከትሎ የጸጥታ ችግር መከሰቱን ተናግረዋል፡፡ “የተደራጀ ቡድን” ያሉት ኃይል የቡድን መሳሪያ ተጠቅሞ ጥቃት ማድረሱንም ኀላፊው አንስተዋል፡፡ በዚም ሰዎች ሞተዋል፤ ቆስለዋል፤ ሀብትና ንብረትም ወድሟል፤ የመንግሥት ተቋማትም ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው ያሉት ኃላፊው፡፡

ድርጊቱ የፖለቲካ መዋቅሩን፣ የፖለቲካ መሪዎችን እና ሕዝቡንም ያሳዘነ ነው ብለዋል፡፡ በአካባቢው የጸጥታ አካላት ለመመከት ጥረት መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡ ነገር ግን ጥቃቱ በቡድን መሳሪያ የታገዘ በመሆኑ ባለው ኀይል ብቻ መመከት እንዳልተቻለም ጠቅሰዋል፡፡ ተጨማሪ የጸጥታ ኀይል እስኪገባ ግን የአካባቢው ፖሊስ፣ ሚሊሻና የአማራ ልዩ ኀይል ጥቃቱን ለማስቆም ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

አሁን ግን ተጨማሪ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና የፌዴራል ፖሊስ መግባቱን የገለጹት አቶ ሲሳይ ትናንት (መጋቢት 11/2013 ዓ.ም) አጣዬ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት ጥረት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የታጠቀው ቡድን እስካሁን ድረስ ተኩስ መግጠሙን ያመላከቱት አቶ ሲሳይ ጥቃቱን ወደ ማጀቴ፣ ሰንበቴና ሸዋሮቢት አካባቢዎች ለማስፋት እሞከረ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የክልሉ የጸጥታ መዋቅር ወደ ቦታው አቅንቶ ከሰሜን ሸዋ የሥራ ኀላፊዎች ጋር እየሠራ አንደሆነም ገልጸዋል፡፡ አቶ ሲሳይ እንዳሉት በሽብር ቡድኑ ላይ ሕግ የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ እጃቸው ያለበትን አካላት ለሕግ አቅርቦ ተጠያቂ ለማድረግም እየተሠራ ነው፡፡

ቢሮ ኀላፊው እንዳሉት ሁኔታዎችን በአግባቡ መምራት ያስፈልጋል፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በስሜት ሳይሆን በሰከነ መልኩ ወቅቱን መሻገር እንዳለበትም መክረዋል፡፡ “ሆደ ሰፊ እንሁን ስንል የአማራ ሕዝብን አሳልፈን እንስጥ ማለት አይደለም” በማለትም ሕዝቡ ትእግስት በተሞላበት አግባብ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ቢሮው በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈጠረውን ችግር ማን እንደፈጠረው፣ ምን ጉዳት እንደደረሰ በቀጣይ እያጣራ ለሕዝብ እንደሚገልጽ አስታውቀዋል፡፡(አብመድ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top