Connect with us

“እየተከታተልነው ነው!” የውጭ ጉዳይ ሚ/ር

"እየተከታተልነው ነው!" የውጭ ጉዳይ ሚ/ር
የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ዜና

“እየተከታተልነው ነው!” የውጭ ጉዳይ ሚ/ር

“እየተከታተልነው ነው!” የውጭ ጉዳይ ሚ/ር

በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ በነበሩ ኢትዮጵያውን ዜጎቻችን ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የተሰጠ ፕሬስ መግለጫ

የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ ማቆያ እስር ቤት ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ በእስር ቤቱ ውስጥ በነበሩ እስረኞች ላይ የሞትና የቁስለት አደጋ እንደደረሰ በሙስካት (ኦማን) የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ ለኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

የአደጋው መንስኤ የሳት ቃጠሎ ሲሆን የቃጠሎው መነሻ ከየመን ተፋላሚዎች ጋር የተገናኘ ስለመሆኑ፣ ምንያህል ሰዎች እንደተጎዱና ምን ያህሉ ኢትዮጵያውን እንደሆኑም በኤምባሲው በኩል እየተጣራ ሲሆን መንግስት በትኩረት እየተከታተለው ያለ ስለሆነ የተረጋገጠ መረጃ እንደደረሰ ይፋ የሚደረግ ይሆናል። 

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደረሰው የእሳት አደጋ ምክንያት ለጠፋው የዜጎቻችን ሕይወትና ለደረሰው የአካል ጉዳት ከፍተኛ ሃዘን እንደተሰማው በመንግስት ስም እየገለጸ ፤ጉዳቱን ያከፋውና ሙሉ መረጃም ለማግኘት አዳጋች ያደረገው ዜጎች በህገወጥ መንገድ ያደረጉት ጉዞ  እንደሆነ ይገነዘባል። በመሆኑም ዜጎች ወደ ውጭ አገራት ጭምር በነጻና ሕጋዊ መንገድ የመንቀሳቀስ መብታቸው በሕገ መንግስቱ የተደነገገ መብት ቢሆንም በሕጋዊና ሕጋዊ መንግድ ብቻ ከሃገር ለመውጣት ቢሞከሩ መሰል አደጋዎችንና የዜጎቻችንን መብት ለማስከበር ይረዳል።

ከዚህ አንጻር መንግስት ከተለያዩ አገራት ጋር በዋናነትም ከመካከለኛው ምስራቅ አገራት ጋር የተለያዩ የአሠሪና ሠራተኛ ውሎችን ተፈራርሟል፤ እየተፈራረመም ይገኛል። ዜጎቻችን ለሥራ ጉዳይ ወደ ውጭ አገራት የሚያደርጉትን ጉዞ በዚህ ሕጋዊነትን በተላበሰ መስመር ቢወጡ ለራሳቸው ህይትም ሆነ ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ ያስችላል።

መንግስት ትናንት በሰንዓ በተከሰተው ክስተት የተጎዱ ዜጎቻችን በደረሰባቸው አደጋ የተሰማውን ልባዊ ሃዘን በድጋሚ እየገለጸና በአደጋው የተጎዱ ዜጎቻችንን ብዛትና የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ክትትሉ የቀጠለ መሆኑን እየገለጸ ሙሉ መረጃው እንደደረሰው ለህዝብ የሚያሳውቅ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።

የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top