Connect with us

#የኦነግ_ቅሬታ!

#የኦነግ_ቅሬታ!
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

ነፃ ሃሳብ

#የኦነግ_ቅሬታ!

#የኦነግ_ቅሬታ!

በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የምርጫ ጉዳዮችን በተመለከተ በኦነግ የተሰጠ የፕሬስ መግለጫ

ኦነግ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረገዉ ስምምነት ለአስርት አመታት የቆየውን ጠላትነት ነሐሴ 2010 ዓ.ም አቋርጦ የኦሮሞን ህዝብ የዲሞክራሲ እና የራስን እድል በራስ የመወሰን ጥያቄ ቀጣይ ምዕራፍ በሰላማዊ መንገድ የፓለቲካ ትክል ለማከናወን መስከረም 2011 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የኦነግ አመራር መመለሱ ይታወሳል፡፡ 

በወቅቱ ህዝባችን አገሪቷ ከሚያዝያ 12/2018 እ.ኤ.አ ጀምሮ የገባችበትን የሁለት አመት የሽግግር ሂደት መጠናቀቅን ተከትሎ በአገሪቷ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ ይካሄዳል የሚል እምነት ነበር፡፡

ነገር ግን እነዚህ ተስፋዎች ማቆልቆል ጀምረው ወደ ባዶ ደረጃ የወረዱት ብዙም ረዥም ጊዜ ሳይቆዩ ነበር፡፡ ተቃዋሚ “የፓለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር እንዲገባ መፍቀድ” የሚለውን ባነር ባነገበ ገዢ ቡድን ርካሽ የፓለቲካ ድል ግብ ከዋለ በኋላ ስርዓቱ ምንም ጊዜ አላባከነም፡፡ ኦነግ በመስከረም 5 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በጥቂት ቀናት ውስጥ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በማህበራዊ እና በመደበኛ ሚዲያ አማካይነት ይደረግበት ጀመር፡፡

በእነዚህ የፕሮፖጋንዳ ጥቃት እና መረጃ ማሳሳት ዘመቻ ጫፍ ላይ እንዲሁም በኦነግ በኩል ውይይት እንዲደረግ ጥረቶቸ ቢደረጉም ስርዓቱ በምዕራብ እና በደቡብ ኦሮሚያ ክፍሎች የወታደራዊ ዘመቻ ውስጥ ገብቷል፡፡ በነሐሴ 2010 ዓ.ም በተደረገው የአስመራ ስምምነት ላይ በተስማሙት መሰረት ጦርነቱ እንዲያበቃ እና የኦነግ ሰራዊት የክልሉ ፖሊስ እና የደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ እንዲዋሃዱ የተደረሰውን ስምምነት ስርዓቱ ፈፅሞ ያልፈለገ መሆኑን  አሁን በግልፅ የታየ ጉዳይ ነው፡፡ 

የነፃነት ታጋዮቹ ከማህበረሰቡ ጋር በማዋሃድ እና ወታደራዊ የትጥቅ ትግሉን በተሳካ ሁኔታ ከማቆም ይልቅ ስርዓቱ ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ከሚያደርገው የፓለቲካ ትግል ከታጠቁት ሽምግ ተዋጊዎች ጋር የሌለውን ግንኙነት አለው ብሎ በሀሰት በመወንጀል ከሰላማዊ ትግሉ ለመግፋት እንደመሳሪያ መጠቀምን መርጧል፡፡

የሚጠበቀው የነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም ምርጫ ከመደረጉ በፊት ተቃዋሚዎችን በኦሮሚያ ውስጥ የማዳከም ስራው ቀጥሎ በተፋፋመበት ሁኔታ የኮቪድ 19 በሽታ ተከስቷል፡፡ 

በሽታው በአገር አቀፍ ደረጃ ምርጫን ለማካሄድ አስቸጋሪ የሆኑ የተለያዩ ሁኔታዎችን ፈጥሮ እያለ ይህንን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ምርጫውን በተለያዩ የህግ እና የፓለቲካ ሂደቶች እንቅፋት ውስጥ ገብቷል፡፡ በህጋዊ መንገድ ሲታይ ህገመንግስቱ የፓርላማ አባላት የስልጣን ዘመን ገደብ ለማራዘም ምንም አይነት ክፍተት ያልፈጠረ ቢሆንም የምርጫን ማስተላለፍ ጉዳይ ባሉት የፓለቲካ ሀይሎች አዲስ የፓለቲካ ውሳኔ መወሰንን ያስፈልገዉ ነበር፡፡ 

ይሁንና ገዢው መንግስት እነዚህን ሀይሎች ያለምንም ጥርጥር በውሳኔው ላይ እንዳይሳተፉ አድርጓል፡፡

ይህንን ህገወጥ የስልጣን ማራዘም ተግባርን ለመቃወም እና ውድቅ የማድረግ ሂደት ከሁሉም አቅጣጫ በመፋፋሙ ምክንያት ገዢው ስርዓት በአሁኑ ጊዜ በግራ ዘመም ፣ በቀኝ ዘመም እና በመሀል ሰፋሪ የተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ተቃዋሚዎችን የመስበር ሂደቱን የበለጠ ለማስቀጠል ብሩህ ልጃችን የሆነውን አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ እንደ መሳሪያ ተጠቅሟል፡፡ እስካሁን ድረስ የሀጫሉ እና የብዙ የሌሎች ከፍተኛ የፓለቲካ ግድያ ድርጊቶች በገለልተኛ ሶስተኛ ወገን አልተመረመረም፡፡

በአገሪቱ የደቡብ አጋማሽ ላይ የክልል ራስ-ገዝነት እና የራስን እድል በራስ የመወሰን ፓለቲካን በሚያራምዱ ሁሉም ሀይሎች ላይ እንደዚህ አይነቱን ከባድ የመበታተን እና የመሰባበር ተግባር በመፈፀም ገዢው ፓርቲ በፓለቲካ ድርድር እና ውይይት ከመፍታት ይልቅ የፓለቲካ  ልዩነት በላቸው ወገኖች ላይ በትግራይ ክልል የኦሮሚያ እና የሰፊው ደቡብ የአገሪቱ ክፍል ላይ የተፈፀመው የመበታተን ስራ ቀጣይ የሆነውን ጦርነት ከፍቷል፡፡ 

ኦነግ የህውሀት ዝምድና እንደሌለዉ ህብረተሰቡ የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ እኛ ከግብራበሮቻችን ጋር በመሆን ህውሃትን ከስልጣን ለማስወገድ እንዲሁም አሁን አቋም በሌለው የኢህአዴግ መንግስት ላይ ትግል ስናካሂድ የነበርን ግንባር ቀደም የፓለቲካ ድርጅት ነን፡፡ ነገር ግን በመርህ ደረጃ አሁን በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለው ጦርነት ኦሮሚያ ውስጥ ሲፈፀም ከነበረው ጭቆና ተስፋፍቶ የተዛመተ ጦርነት ነው ብለን እንገነዘባለን፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይን በተመለከተ በድርድር ለመፍታት ለአሜሪካ ገዢው ፓርቲ ስምምነት ደርሶ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስህተት ከተፈፀመ በኋላ ኢትዮጵያ አጋሯን ሱዳን ያጣች ሲሆን እኛ አሁን ከሌላዋ የጎረቤት አገር ጋር ጦርነት ልንጋጠም አፋፍ ላይ እንገኛለን፡፡

ከፍተኛ የፓለቲካ አመራሮችን ጨምሮ የዋና ዋና ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች አባላት በገዢው  ፓርቲ በዘፈቀደ ተይዘው የሚታሰሩበት፤ በፍርድ ቤቶች ወይም በመንግስት አቃቤ ህግ መስሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ነፃ ተብሎ በሚለቀቁበት ጊዜ ጨምሮ በከፍተኛ አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ እንዲቆዩ የሚደረግበት ሁኔታ የሚስተዋልበት አገር ውስጥ እየኖርን እንገኛለን፡፡  

የተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች ጽ/ቤት – ከዋና መስሪያ ቤቶቻቸው ጨምሮ በዘፈቀደ በገዢው ፓርቲ ተወሮ የሚያዝበት አገር ውስጥ እየኖርን እንገኛለን፡፡

እንግዲህ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆና ነው አገሪቷ ለአቀር አቀፍ አጠቃላይ ምርጫ “እየተዘጋጀች” ትገኛለች፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው እያንዳንዱ አባላት ምርጫ ማለት የምርጫ ካርድ በኮሮጆ ውስጥ ስለምንከትበት ቀን የምናወሳበት ሂደት ብቻ አለመሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን፡፡ 

የምርጫ ጠቃሚው ጉዳይ ወደ ምርጫው ቀን የሚመራው ሂደት ነው፡፡ የዲሞክራሲ ስርዓትን ለመዘርጋት የመአዘን ድንጋይ የሆነው የምርጫው ተአማኒነት በአብዛኛው የሁሉም የቅድመ ምርጫ ሂደቶች እና ተግባራት ላይ የሚወሰን ሲሆን ይህም ለተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን የሚገልፁበት የተደላደለ ሜዳ መኖርን ያካትታል፡፡ 

ምርጫ በአጠቃላይ የምርጫ ካርድን በሚስጥር ወደ ኮሮጆ ወስጥ ወደመክተቻ ቀን የሚያመሩትን ሂደቶች በአጠቃላይ የሚስተዋሉበት ሁኔታ ላይ ተመስርቶ የሚወሰን መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የምርጫ ሂደት ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ ነው ተብሎ እንዲወሰን የሚያደርግ ሂደት ላይ የሚመረኮዝ ነው፡፡ 

ይህ ሂደት በፓለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን እና ስራቸውን በነፃነት እንዲያሳውቁ፣ ለሁሉም ያለምንም አድሎ የሚያገለግል ገለልተኛ ሚዲያ መኖር፣ የምርጫ ቦርድ እና የፍትህ አካላት ገለልተኛ ሆነው ማገልገልን የሚፈቅድ ቦታ የሚያዘጋጅ መሆን አለበት፡፡

ምርጫው ፍትሐዊ ገለልተኛ እና ተአማኒነት ያለው ለመሆነ ያነሰ እድል ያለው በመሆኑ ይህ ምርጫ ውጤቱ አስቀድሞ የታወቀ ምርጫ ነው፡፡ ለገለልተኛ ታዛቢ ከታየ ይህ ምርጫ እነዚህን መስፈርቶች አሟልቶ ያልቀረበ ፍፁም ምርጫ ሊባል የማይችል ተግባር ነው፡፡ ገዢው ቡድን ይህንን ምርጫ ለማካሄድ የወሰነበት ብቸኛ ምክንያት በምርጫ ተመርጦ ስልጣን ላይ የወጣ መንግስት ለማስመሰል ብቻ ነው፡፡ 

ከዚህ ውጪ በዛሬው ቀን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቹ ለሚራብ ድሃ አገር ይህ አይነቱ በለጋሾች እና ባለሀብቶች ልገሳ የሚካሄደው ውድ ምርጫ ለማካሄድ ምንም ምክንያት የለም፡፡

ከዚህ የተነሳ ኦነግ የሚከተለው እምነት አለው፡

  1. በዲሞክራሲ ስርዓት ውስጥ የሚደረግ ነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስፈልጉ ዝቅተኛ መስፈርቶችን ማሟላት ይቅርና የአገሪቷ የአሁኑ ገዢ መንግስት በሌላው አገር የሚታዩ ነፃ ያልሆኑ የዲሞክራሲ ዝቅተኛ ደረጃዎችን እንኳን አያሟላም፡፡
  2. ባለፉት 2 አመታት ከላይ በተጠቀሱት ሂደት ውስጥ በከፊል በመንቀሳቀስ የዚህ አይነቱ ምርጫ ውጤት ነፃ እና ፍትሐዊ ያልሆነ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ውክልና እና ተቀባይነት የሌለው ይሆናል፡፡
  3. ምርጫው ከተካሄደም የአገሪቷን ዋና ዋና የፓለቲካ ችግሮች እና የግጭት ምንጮች የሆኑትን ችግሮች በመፍታት ረገድ ምንም አይነት ይህ ነው የተባለ ልዩነት አያመጣም፡፡

ኦነግ ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ሆን ብሎ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ለማሟላት ሆን ብሎ ያልፈለገ እንዲሁም ለራሱ እና ለአጋሮቹ በምርጫ ውስጥ የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት ሲባል ጆሮ ዳባ ልበስ ያለ በመሆኑ እና ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ለማሟላት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት ለመሳተፍ ያልቻለ መሆኑን ሲገልፅ ሀዘን ይሰማዋል፡፡

ተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ሰፊው ህዝብ የሚፈልገውን የሚከተሉትን ህጋዊ ጥያቄዎች ለማሟላቱ እና ለአገሪቱ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚያግዙ መስፈርቶችን ተግባራዊ ማድረግ ለሃገሪቱ ይጠቅማል ብለን እናምናልን፥

  1. ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሁሉንም የፓለቲካ እስረኞችን መልቀቅ
  2. በገዢው ፓርቲ እና እርሱ በሚቆጣጠረው የደህንነት ሀይሎች በአሁኑ ጊዜ የተዘጉ እና/ወይም በቁጥጥር ስር ያሉትን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጽ/ቤት መልሶ መክፈት
  3. በአገሪቱ ሁሉም ክፍሎች የሚስተዋሉትን ሁሉም ጦርነቶች በማቆም ሁሉን ያካተተ ድርድር እንዲደረግ
  4. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የዳኝነት ስርዓት እና የህግ አስፈፃሚ አካልን ጨምሮ ቁልፍ የሆኑ ተቋማትን ገለልተኝነት እና ከአድሎ የፀዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ
  5. ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የፖለቲካ ለዩነቶችን ለመፍታት ያለመ ወሳኝ የፓለቲካ ውይይት ሂደት ማስጀመር

ድል ለሰፊው ህዝብ

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር

የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top