Connect with us

ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር በመውረር የአፍሪካ ቀንድን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ጥላለች- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር በመውረር የአፍሪካ ቀንድን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ጥላለች- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Fana Broadcasting Corporate S.C

ዜና

ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር በመውረር የአፍሪካ ቀንድን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ጥላለች- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር በመውረር የአፍሪካ ቀንድን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ ጥላለች- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታ (ኢጋድ) ሊቀመንበር ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር በመውረር የአፍሪካ ቀንድን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ላይ መሰማራቷ የሚያሳዝን ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሱዳን ምንም እንኳን የኢጋድ ሊቀመንበር ብትሆንም የኢትዮጵያን መሬት ወራ፣ ሰላማዊ ዜጎችን አፈናቅላ አሁንም ተጨማሪ መሬቶችን ለመውረር የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመች ነው ብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሱዳን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር እርምጃ ሲሰማራ ከወረረችው የኢትዮጵያ መሬት ሰራዊቷን እንድታስወጣ እና ወደ ራሷ እንድትመለስ ጫና እንዲፈጥር በትዊትር ገጹ ላይ በማሰፈረው ፅኁፍ ጥሪ አቅርቧል ።

ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 1972 የማስታወሻ ልውውጥ መሰረት የድንበር ልዩነቱን በግጭት መፍቻ መንገዶች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል።(FBC)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top