Connect with us

11 ሆቴሎች ተሸለሙ

11 ሆቴሎች ተሸለሙ
የባህልና ቱሪዝም ሚ/ር

ዜና

11 ሆቴሎች ተሸለሙ

11 ሆቴሎች ተሸለሙ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ፕሮቶኮሎችን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ላደረጉ ሆቴሎች እውቅና ሰጠ።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በወርሀ መጋቢት ወደ ሀገራችን ከገባ ጀምሮ ጉዳት ከደረሰባቸው ዘርፎች  የቱሪዝም ዘርፍ አንዱ ሲሆን   በሀገራችን የሚገኙ ሆቴሎችም የዚሁ ችግር ሰለባ በመሆናቸው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ይህንን ችግር ለመቅረፍ  የኮቪድ ፕሮቶኮል በማዘጋጀት ወደ ስራ ከገባ ወራትን አስቆጥረዋል። የዚህ ፕሮቶኮል አንዱ አካል የሆነው ሆቴሎችን  ምዘና በማድረግ እውቅና የመስጠት ፕሮግራም የተዘጋጀው።

በእውቅና አሠጣጥ ሥነሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው እንዳሉት ወረርሽኙ ወደ ሀገራችን መግባቱ ሲሰማ ሆቴሎች የነበራቸው ስጋት ከፍተኛ እንደነበር ተናግረው ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን ችግሮችን የመቋቋም ባህል እንዳለን የተመሠከረልን መሆናችንን በተግባር ሆቴሎቻችን ማሳያ ናቸው ብለው ይህንን ችግር በመቋቋም ሆቴሎቻቸውን ሳይዘጉ  አገልግሎቶችን መቀጠላቸው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና በራሳቸው ስም ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የገቡት ሆቴሎች የኮሮና ቫይረስን በመከላከል አገልግሎቶችን እንዲያስቀጥሉ የወጡ ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ፕሮቶኮሎች መካከል የሆቴል አገልግሎት አቅርቦት የመልሶ ማቋቋም ፕሮግራም የደህንነት እና የጥንቃቄ ስትራቴጂን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ላደረጉ እውቅና ይገባቸዋል ብለው በቀጣይም ከሆቴሎች የሚጠበቀው ተግባር ይህ ብቻ እንዳልሆነ ተናግረው በቀጣይም ከዚህም በበለጠ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

በዚህ መርሐ ግብር 16 ሆቴሎች ምዘና ተደርጎላቸው 11 ሆቴሎች ለመጀመሪያ ዙር የእውቅናውን ሠርተፊኬት ተሰጥቷቸዋል ። የተቀሩት 5 ሆቴሎች የተሰጣቸውን ማስተካከያ አድርገው በቀጣይ ቀናት እውቅና ይሰጣቸዋል። በቀጣይም በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልሎችም እንደሚቀጥል አዘጋጅ ኮሚቴው አሳውቋል። በፕሮግራሙም የእውቅና ሠርተፊኬት ካገኙት ሆቴል መካከል አንዱ የሆነውን   የካፒታል ሆቴል የኮቪድ ፕሮቶኮል አፈፃፀም ስራ በተሳታፊዎች ተጎብኝቷል።(የባህልና ቱሪዝም ሚ/ር)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top