Connect with us

እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ዛሬም ችሎት አልቀረቡም

እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ዛሬም ችሎት አልቀረቡም
Photo: Social media

ወንጀል ነክ

እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ዛሬም ችሎት አልቀረቡም

እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ዛሬም ችሎት አልቀረቡም

አቶ ጃዋር መሃመድና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬም በቀጠሮአቸዉ ችሎት አለመገኘታቸዉ ተገለፀ። ሁሉም ተከሳሾች ለዛሬው ኅዳር 15 ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ አስተላልፎ የነበረ ቢሆንም አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬም በችሎቱ ላይ አልተገኙም፡፡ ከሁለቱ ፖለቲከኞች በተጨማሪም አቶ ሃምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲን ጠሃም ከዛሬው ችሎት ቀርተዋል፡፡

ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት “ሁከትን በማነሳሳት” ወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ክስ የቀረበባቸዉ አቶ ጃዋር መሃመድ  አቶ በቀለ ገርባ እና በመዝገቡ ስር የተጠቀሱ ተጠርጣሪዎች የንብረት እገዳን በተመለከተ ጥቅምት 17 እና 24 ከተከሳሾች እና ዐቃቤ ሕግ በኩል ክርክራቸውን የሰማው ፍርድ ቤት ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ህዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዞ ነበር። 

ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው በንብረት እገዳው ላይ ተከራክረው የነበሩት አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ላይ “የደህንነት ስጋት” በማለት ሳይቀርቡ መቅረታቸዉ ይታወቃል።  

የተከሳሾች ጠበቆች ከታገዱት ንብረቶች ውስጥ ለወንጀል ምርመራው ምንም አይነት ጥቅም የሌላቸውም ነገሮች ጭምር መያዛቸውንና እነዚህ ንብረቶች መለቀቅ አለባቸው በሚል ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱ ለወንጀል ምርመራው የማይጠቅሙ ንብረቶች እንዲለቀቁ ሲፈቅድ ዐቃቤ ህግም በጽሁፍ ተጠይቀው ምላሽ እንደሚሰጥባቸው ማሳወቁን ጠበቃ ከድር ቡሎ ገልፀዋል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን እንደገና ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት ለኅዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶኣል። 

በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ማግስት በቁጥጥር ስር የዋሉት እነ አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 24 ተከሳሾች በ1996 የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 240ን በመተላላፍ ብሔር እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ግጭት ቀስቅሰዋል በሚል እና በሌሎች የሽብር ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ እንደመሰረተባቸው ይታወሳል፡፡

 

( ስዩም ጌቱ ~ ጀርመን ድምፅ)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top