Connect with us

ከፍተኛ የብረታብረት ክምችት ተያዘ

ከፍተኛ የብረታብረት ክምችት ተያዘ
ፌ/ፖሊስ

ወንጀል ነክ

ከፍተኛ የብረታብረት ክምችት ተያዘ

ከፍተኛ የብረታብረት ክምችት ተያዘ

በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ በርካታ ብረታ ብረት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

አሸባሪው የህዋሓት ጁንታ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስና የሀገር ማፍረስ እኩይ ተልዕኮውን ለማሳካት የተለያዩ የኢኮኖሚ አሻጥር መረቦችን ዘርግቶ ሲሰራ መቆየቱን ፖሊስ በምርመራ ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡

እነዚህ ብረታ ብረቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዴት ሊገቡ እንደቻሉ የጉምሩክ ባለሙያ የሆኑት አቶ ረጋሳ ጊቲ  በተደረገላቸው ቃለ-መጠይቅ ከቀረጥ ነፃና በቀረጥ በህጋዊ መንገድ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገቡ  ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ እንዳስታወቁት በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ በ17 መጋዘኖችና በተለያዩ ስፍራዎች ተደብቆ የነበረ በብዙ ቢሊዮን ብር የሚገመት የብረታ ብረት ክምችት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ፖሊስ ከህዝቡ የደረሱ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንና ከሌሎች የፀጥታ  አካላት ጋር በመቀናጀት ሰሞኑን ባደረገው ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ገልፀዋል፡፡ በዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎችንም በመያዝ ፖሊስ የምርመራ ስራውን አጠናክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ምክትል ኮሚሽነር አመልክተዋል፡፡

ጁንታው የሀገርን ኢኮኖሚ ለማዳከም ከሚያከናውናቸው እኩይ ተግባራት አንዱ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጫና በማሳደርና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመፍጠር ህዝብና መንግስትን ማጋጨት ዋነኛው ግቡ አድርጎ ሲንቀሳቀስ እንደነበር ም/ኮሚሽነር ጀነራሉና የጉምሩክ ኮሚሽን ባለሙያ ተናገረዋል፡፡

አሸባሪው የህወሃት ጁንታ በትግራይ ክልል በኢንቨስትመንት ስም ሆቴሎችን፣ ፎቆችን፣ ድልድዮችንና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን እንሰራለን በሚል በመንግስት ውሳኔ ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋቸውንና በርካታ የውጭ ምንዛሬ የወጣባቸውን ብረታ ብረትና ሌሎች የልማት ቁሳቁሶችን በህገ-ወጥ መንገድ በማከማቸት በስራ ላይ እንዳይውሉ ማድረጉ ወንጀል መሆኑን ፖሊስ  አመልክቷል፡፡

ፖሊስ ባደረገው የተጠናከረ የማጣራትና የፍተሻ ስራ ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር በላይ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ተደብቆ መገኘቱ እና ከአሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድን ጋር ህብረት ፈጥረው በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ላይ የሚሳተፉ አካላትን በመያዝ ፖሊስ የምርመራ ስራውን እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጿል።(ፌ/ፖሊስ)

 

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top