Connect with us

የሠረገላ ታክሲ አሽከርካሪዋ ላይ የውንብድና ወንጀል የፈጸሙት በእስራት ተቀጡ

የሠረገላ ታክሲ አሽከርካሪዋ ላይ የውንብድና ወንጀል የፈጸሙት በእስራት ተቀጡ
የፌ/ጠ/ዐ/ህግ

ወንጀል ነክ

የሠረገላ ታክሲ አሽከርካሪዋ ላይ የውንብድና ወንጀል የፈጸሙት በእስራት ተቀጡ

የሠረገላ ታክሲ አሽከርካሪዋ ላይ የውንብድና ወንጀል የፈጸሙት በእስራት ተቀጡ

ቢንያም ተስፋዬ እና እዮብ ፋንታሁን የተባሉ ተከሳሾች በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ እና 671/1/ሐ ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የማይገባቸውን ብልፅግና ለራሳቸው ለማግኝት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኝት በማሰብ መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 4፡00 ሰአት ሲሆን በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው አርሴማ ድልድይ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የግል ተበዳይ ስርጉት ደጉ የሰረገላ ታክሲ እያሽከረከረች ባለችበት ሰዓት ተከሳሾቹ  ወደ ኮዬ ፈጬ አቅጣጫ የትራንስፖርት አገልግሎት እንድትሰጣቸው በመጠየቅ ከተሳፈሩ በኋላ  በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው አርሴማ ድልድይ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ አውርጂን በማለትና በማስቆም እዮብ ፋንታሁን የተባለው ተከሳሽ የግል ተበዳይን አንገት በእጁ አንቆ ወደኃላ ሲይዛት ቢንያም ተስፋዬ የተባለው ተከሳሽ ደግሞ የግል ተበዳይን J2 ሳምሰንግ ሞባይል የዋጋ ግምቱ 5ሺ ብር የሆነውን ቀምቶ መኪና ውስጥ በነበረ ቻርጀር ኬብል ሁለት እጇን አጣምሮ ካሰራት በኋላ ጥለዋት የሄዱ በመሆኑ በቁጥጥር ስር ውለው በዐቃቤ ህግ ከባድ ውንብድና ወንጀል ክስ ተመስርቶባችዋል፡፡

በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎትም በዐቃቤ ህግ የቀረበለትን ክስ በሰውና በሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ተከሳሾች እንዲከላከሉ ብይን ቢሰጥም መከላከያ የለንም በማለታቸው በተከሰሱት የህግ ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ ናቹ በማለት መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾች እያንዳዳቸው በአምስት አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡(የፌ/ጠ/ዐ/ህግ)

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top